‹በኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ›

ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ ገለጹ።
ዶክተር ሊያ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
በአንድ ቀን ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሦስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe