ኢትዮጵያ ከምግብና ሥርዓተ ምግብ ጋር በተያያዘ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ( #GDP ) 16 በመቶውን እያጣች ነው፡፡
እድሜያቸው 5 ዓመት በታች ከሆናቸው አንድ መቶ ህፃናት 36ቱ የቀነጨሩ መሆናቸውን ከ6 ዓመት በፊት የተጠና ጥናት ያሳያል፡፡
የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣት ፣የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ፣የግብርና አለመዘመን ፣ብክነት ተደማምረው የምግብ እና የስርዓተ ምግብን ጉዳይ እንዲፈተን አድርገውታል፡፡
የአለም መንግስታት ከ5 ዓመታት በኋላ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2030 ላይ እናሳካቸዋለን ብለው ከያዟቸው ዘላቂ የልማት ግቦች መካከል አንደኛው ይሄው የምግብ ስርዓት ዋነኛው ነው፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኞቹ ሃገራት በዚህ ዘርፍ ለመስራት ካስቡት ማሳካት የቻሉት 10 በመቶውን ብቻ ነው፡፡
በመጪው 5 ዓመታትም ሙሉ በሙሉ ያሳኩታል ተብሎ አይገመትም፡፡
ይህን የምግብ ሥርዓት ጉዳይ በእጅጉ ከሚፈትኑት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው የአየር ንብረት ለውጥ ነው።
ኢትዮጵያ በዚህ ብዙ አጥታለች፣ ተጎድታለች፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት ለውጥ አስተባባሪ የሆኑት ከፈለኝ ጌታሁን (ዶ/ር ) ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶችን ጠቅሰው የደረሱ ጉዳቶችን ያስረዳሉ ፡፡
ባለፉት 20 ዓመታት በአርብቶ አደር አካባቢ የ35 በመቶ ውሃ መቀነስ ታይቷል፡፡
ጥናቱ ከ10 ዓመት በፊት የተሰራ ጥ ነው፡፡
የአንሳሳት ሀብት፣ ለምሳሌ ከዛሬ 8 አመት በፊት በነበረው ኤልኒኖ ወደ 1.5 ሚሊዮን ከብቶች ሞተዋል፡፡
ምርታማነት ላይም ተጽኖ ነበረው፡፡
ከአገራዊ ምርት ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ግብርና ነው፡፡
የ1977 ድርቅ ብናይ ለምሳሌ ድርቁ የአገሪቷን 10 በመቶ ሃገራዊ ምርት ወስዶታል፡፡
ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ዋነኛ ገፈት ቀማሽ ብትሆንም በአለም ላይ በካይ ጋዝን በመልቀቅ ያላት ድርሻ 0.02 በመቶ መሆኑን ከፍለኝ (ዶ/ር) መረጃዎችን ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡
በዚህም በካይ ሀገራት ካሳ እንዲከፍሉ ብዙ ሲጠየቅ ቢሰማም ብዙ አትሳካም፡፡
ታዲያ ተጎጂዋ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተጽኖን ለመቀነስ ምን ማድረግ ትችላለች ያልናቸው ከፈለኝ ጌታሁን ( ዶ/ር) ይሄን ያስረዳሉ፡፡
“አንግዲህ እኛ የቤት ስራችንን እየሰራን ነው፡፡ ዲፕሎማሲ ብዙ ዘርፍ ነው ይሄ ነገር እኛ ብቻ አይደለም በዚህ ተጋለጭ፡፡
ለምሳሌ እንደነ ማልዲቭስ ያሉት ሀገራት ከኛ የበለጠ ችግር ውስጥ” ነው ያሉት፡፡
ባለፈው COP 29 ላይ ወደ 300 ቢሊየን ዶላር ጠይቀዋል፡፡ ብዙ አገሮች ራሳቸውም እነ አሜሪካ ፣ቻይና አየር ንብረት ለውጥ እየተፈተኑ ነው፡፡ እውነታውን እያወቁት ነው ይሄን ነገር ገሸሽ የሚያደርጉት፡፡
እነሱ ከፍተኛ ግሪን ሃውስ ጋዝ እያመነጩ፣ የድንጋይ ከሳል ተጠቅው ነው ብዙዎቹ ያደጉት፡፡
የአውሮፓ ሀገሮችም ስለዚህ ይሄ ድርድር መቀጠል መቻል አለበት። ግን ያ ማለት እነሱ አስከሚያደርጉት መጠበቅ የለብንም፡፡ የራሳችንን ስራ እየሰራን ነው፡፡
የአየር ንብረት ተፅዕኖ አለም አቀፋዊ ቢሆንም ዝም ብለን ከምንቀመጥ የራሳችንን ስራ እየሰራን ነው፣ይህ ደግሞ እያዋጣን ነው፡፡
ቢያንስ የራሳችንን የቤት ስራ እየሰራን፣ በእዛኛው አቅጣጫ ደግሞ ጉዳዩ አለም አቀፋዊ ስለሆነ እነሱም ተፅዕኖውን እያዩት ስለሆነ ይመጡበታል ብለን እንጠብቃለን፡፡
የምግብ ስርዓትን መልክ ለማስያዝ የጤና እና የግብርና ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚመሩት 16 ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ያሉበት ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡
የሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት ፣ግሪን ሌጋሲ፣ የትምህርት ቤት ምገባ ፣የሌማት ትሩፋት ይመሳሰሉት ተነድፋው እየተሰሩ ነው፡፡
ግን ምን ለውጥ መጣ?
እንግዲህ እነዚህ ነገሮች አንዳንዶች በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ ናቸው፡፡
ያመጡትን ተጽኖ በአንድ ጊዜ ማየት ላይቻል ይችላል፡፡ ጥናቶችን ማየት ያስፈልጋል፡፡አካባቢ ላይ የተሰሩ ስራዎች በአንድ ጊዜ ውጤታቸውን ማየት አንዳንዴ አይቻልም፡፡
አንዳንዶቹ ተፅኗቸው ግሎባል ሊሆን ይችላል፣ አንዳንጎቹ ሎካል ሊሆን ይችላል፡፡ እሱን በደንብ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ በተወሰነ ደረጃ ግን ሰዎች እየተቀየሩ ነው፡፡
በዶሮ አንርባታ ፣በአቡካዶ ምርትም ኤክስፖርት የሚደረጉት ከግሪን ሌጋሲ ጋር የተገኛኑ ነገሮች ናቸው፡፡
ቢሾፍቱ፣ አርባምንጭ አካባቢ በተለያዩ አካባቢዎች የሰዎች ገቢ እየጨመረ የአኗኗር ደረጃቸውም እየተቀየረ እንደሆነ እያየን እየሰማን ግው፡፡ይሄ ነገር መስፋት አለበት፡፡”
የዓለም ሀገራት የምግብ ሥርዓታቸውን እንዴት እንዴት እያደረጉት ነው?
የኢትዮጵያስ ምን መልክ አለው? ምንስ ለውጥ እየታየ ነው የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመምክር ውጤቶቹንም ለማየት የተባበሩት መንግስታት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በዚህ ወር መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል፡፡

