ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ህክምና ማዕከላት ከሚያቀኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አብዛኛዎቹ የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ቫይታሚን ዲ በስብ ከሚሟሙ የቫይታሚን አይነቶች አንዱ በተፈጥሮ በጥቂት ምግቦች የሚገኝ ነው፡፡
እነዚህም እንደ አሳ፡የበሬ ጉበት፡የእንቁላል አስኳልና አይብን በመሳሰሉት የምግብ አይነቶች ሲሆን በጸሀይ ብርሃን ደግሞ ሰውነታችን በቂ ቫይታሚን ዲ እንዲያመርት ያደርጋል፡፡
ቫታሚን ዲ በደምና በአጥንት ውስጥ የካልሲየም ሚዛንን ለመጠበቅ፡የአጥንት ግንባታና ጥገናን ለመደገፍ ካልሲየምና ፎስፈረስ እንዲዋሃዱ የሚረዳ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጽያ በርካታ ሰዎች ላይ የቫይታሚን ዲ እየተስተዋለ መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እየገለጹ ነው፡፡ ባለሙያዎቹ ወደ ህክምና ከሚሄዱት ሰዎች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆኑ የቫይታሚን ዲ እጥረት እንደሚገኝባቸውም ተናግረዋል፡፡
የቫይታሚን ዲ እጥረት በነፍሰጡር ሴቶች ላይ የመታየት መጠኑ ከፍ ያለ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

