የኒውክሌር ህክምና በተለይ ለካንሰር በሽታ ህክምና ውጤታማነት የላቀ አስተዋጾ እንዳለው የህክምና ሰዎች ይገላጻሉ፡፡ ነገር ግን በኢትዮጽያ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ከሁለት እንደማይበልጡ የኒውክሌር ህክምና ስፔሻሊስቶች ሃኪሞች ገልጸዋል፡፡
ባለሙያዎቹ ህከምናው በኢትዮጽያ ገና በመዳህ ላይ እንደሚገኝ አንስተው፤በመንግስት የተሰጠው ትኩረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት መግለጻቸውን ከስፑትኒክ ኢትዮጽያ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡
ዘርፉ የህክምና አስተዳደርን ከ30 እስከ 50 በመቶ የመቀየር አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ይህ ማለት የኒውክሌር ህክምና ከሦስት ታካሚዎች የአንዱን፤ከፍ ሲልም የግማሹን የህክምና አሰጣጥ መንገድ የመቀየር አቅም አለው እንደ ማለት ነው ብለዋል፡፡//

