በደቡብ አፍሪካ የ6 ዓመት ልጇን አግታ ሸጣታለች የተባለችው እናት ከሁለት ግበረአበሮቿ ጋር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባታል፡፡
ኬሊ ስሚዝ የተባለችው እናት እንዲሁም ሁለት የወንድ ጓደኞቿ የእድሜ ልክ እስራት የተበየነባቸው ጆሽሊን ስሚዝ የተባለችው ህጻን በኬፕታውን አቅራቢያ ከሚገኘው ቤቷ ደብዛዋ ከጠፋ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው፡፡
የጆሽሊያን መጥፋት በደቡብ አፍሪካዊያን ዘንድ አነጋጋሪ ቢሆንም እስካሁን አልተገኘችም፡፡የፍርድ ሂደቱ ስድስት ሳምንታትን የወሰደ ሲሆን የበርካታ ደቡብ አፍሪካዊያንን ቀልብ የሳበ እንዲሁም ምስክሮችና አቃብያነ ህግ በርካታ አስደንጋጭ ክስተቶችን ይፋ ያደረጉበት ነው፡፡
ዳኛው ናታን ኢራስመስ ሦስቱን ተከሳሾች ያለምንም ልዩነት የዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡ተከሳሾቹ በህገ-ወጥ የሰዎች ማዘዋወር ወንጀል ክስ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
ሦስቱ ተከሳሾች ምንም አይነት ጸጸት አላሳዩም በሚል ዳኛው በከፋ ወቅሰዋቸዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የሚጸጸቱ አይደሉም ያነሰ ቅጣትም ለመፍረድ ምክንያት አላገኘሁም ብለዋል፡፡
የህጻኗ መምሀር በፍለጋው ወቅት ልጇ በኮንቴነር ውስጥ በመርከብ ወደ ምዕራብ አፍሪካ እያቀናች ነው ስትል እናቲቱ መናገሯን ለችሎጹ ገልጸው ነበር፡፡ከዚህ በተጨማሪ ልጄን ገንዘብ ለማግኘት ስል ሸጥኳት ስትል ሰምቻለሁ ያለ ጎረቤት ምስክርነቱን ለችሎቱ አሰምቷል፡፡

