በፑቲን አመራር የስትራቴጅካዊ ኒውክሌር ኃይሎች ልምምድ መካሄዱን ክሬምሊን ገለፀ

በፑቲን አመራር የስትራቴጅካዊ ኒውክሌር ኃይሎች ልምምድ መካሄዱን ክሬምሊን ገለፀ

ተጨማሪ ቁልፍ መግለጫዎች፡-  በሩሲያ ስትራቴጅካዊ የኒውክሌር ኃይሎች ልምምድ ወቅት አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የአየር ክሩዝ ሚሳኤሎች ተወንጭፈዋል፡፡

የያርስ አህጉራዊ ባላስቲክ ሚሳኤል በካምቻትካ ኩራ የሚሳኤል ክልል ከፕሌሴትስክ የጠፈር ጣቢያ ተወንጭፏል።

የስትራቴጂክ የኒውክሌር ኃይሎች ሥልጠና አካል የሆነው የሲኔቫ ባለስቲክ ሚሳኤል ከብርያንስክ የባሬንትስ ባሕር መርክብ ተወንጭፏል።

በሩሲያ ስትራቴጅካዊ የኒውክሌር ኃይሎች ሥልጠና የተሳተፉት ቱ-95ኤምኤስ አውሮፕላኖች የአየር ክሩዝ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፍ ተለማምደዋል፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ ፑቲን በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 ጉባዔ ላይ እንደማይገኙ ክሬምሊን አስታወቀ

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰጧቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፦ የሩሲያን ልዑካን ቡድን ማን እንደሚመራ ክሬምሊን ወደፊት ያሳውቃል።  በፑቲን እና በትራምፕ መካከል ለሚደረገው ስብሰባ ትክክለኛው ቀን ገና አልተወሰነም፤ ሰፊ ዝግጅት ያስፈልጋል።

የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ የሁለቱም ፕሬዝዳንቶች የጋራ ፍላጎት ነው።  ለፑቲን-ትራምፕ ስብሰባ የሚደረገው ዝግጅት መሠረተ ቢስ በሆኑ ብዙ ወሬዎችና ግምቶች የተከበበ ነው።

በፑቲን እና በኦርባን መካከል በአሁኑ ጊዜ ለማድረግ የታሰበ አዲስ የስልክ ውይይት እቅድ የለም።  ሞስኮ የሩሲያ-አረብ ጉባኤ የሚደረግበትን ወቅት አታዘገይም፤ ነገር ግን የጊዜ ሰሌዳዎችን ለማስተባበር ከፍተኛ ሥራ ይቀራል።

Sourcesputnik

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe