ቡርኪና ፋሶ ማሊ እና ኒጀር የጋራ መዝሙር ይፋ ማድረጋቸው ተሰማ

ሦስቱ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ሙዝሙር ይፋ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡

የዓለም መነጋገሪያ የሆነት ካፒቴን ኢብራሂም ትራውሬ የሚመሯት ቡርኪና ፋሶ፡ማሊ እና ኒጀር ናቸው የጋራ ያሉትን መዝሙር ይፋ ያደረጉት፡፡

እነዚሁ ሦስት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከኢኮዋስ ራሳቸውን ካገለሉ ወዲህ ሳህል ስቴት የሚል የሦስትዮሽ ጥምረት ፈጥረዋል፡፡ ይሔው አዲሱ የጋራ መዝሙር የሦስቱ ሀገራት የጋራ ታራካቸውን እና እሴቶቻቸውን የሚያጎላ እንዲሁም የጋራ ምኞቶቻቸውንም ከፍ የሚያደርግ እንደሆነ ነው የተሰማው፡፡

ማሊ፡ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ቀድመው በአባልነት ከነበሩበት የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ኢኮዋስ የተለዩት ከህብረቱ ያጎደልነው ነገር እንጂ ያገኘነው የለም በሚል ነው፡፡ ሀገራቱን ወደ ትብብር ማዕቀፉ ለመመለስ ሲደረግ የነበረው ጥረት ሦስቱ ሀገራት የራሳቸውን አዲስ ጥምረት በመፍጠር ነበር የተጠናቀቀው፡፡

የቡርኪናፋሶው ፕሬዜዳንት ኢብራሂም ትራውሬ በዚህ ወቅት አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስማቸውንን ደጋግመው የሚያነሷቸው  ሰው ሆነው ዘልቋል፡፡ ፕሬዜዳንቱ ከተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎችም እንዳመለጡ ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡

እነዚሁ ሀገራት በቅርብ ጊዚያትም የጋራ ፓስፖርታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe