ቡና ባንክ ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች በልደታ ክፍለ ከተማ፣ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት ድጋፍ አድርጓል፡
ለዚህ በጎ ዓላማ የሚውል የ500,000 ብር የምግብ ዘይት እና የስንዴ ዱቄት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚገኙ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ፣ የ27,000 ብር የምግብ ዘይት – ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ለሚገኙ ዜጎች ፣ እና የ25,000 ብር የስንዴ ዱቄት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች አድርጓል።

በድምሩ የ 552,ዐዐዐ ብር የምግብ ዘይት እና የስንዴ ዱቄት “በማዕድ ማጋራት ” የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአረጋውያን እና ወላጅ አልባ ህጻናት ከክፍለ ከተማ እና የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀት ዛሬ ጳጉሜን 03 2015 ዓ.ም አበርክቷል።

