ቡና ባንክ የነዳጅ ክፍያን በዲጂታል አማራጭ  መከውን ጀመረ

ከነዳጅ አቅራቢዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ተሽከርካሪዎች ጋር በጋራ የሚሰሩ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች የአገራችንን የነዳጅ አቅርቦት ስርዓት በእጅጉ እየለወጠው ይገኛል፡፡

ቡና ባንክም በቅርቡ ከኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በገባው ውል መሰረት ለውጡን መቀላቀሉን አስታወቀ፡፡

ይሄውም ስምምነት ለደንበኞች ግብይቶችን በማሳለጥ ተደራሽነትን ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዲጂታል የክፍያ አማራጮች በመጠቀም የሚከወኑ የነዳጅ ክፍያዎች፣ ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልግ ተያያዥ ስጋቶችንም በመቀነስ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸም ያስችላለ ነው የተባለው፡፡

በቡና ባንክ የነዳጅ ግብይትዎን ሲፈጽሙ፡-

  • አጭርየስልክ ኮድ (USSD Push) በመጠቀም ያለ ኢንተርኔት፣ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል
  • QR Code ንበመጠቀም እንከን-የለሽ አገልግሎት ማግኘት እንዲሁም
  • የማጣቀሻቁጥር ስርዓትን (Reference Number system) በመጠቀም ምቹ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የነዳጅ ግብይቶችን መፈጸም ይችላሉ!
  • ይህ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሸማቾች ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የነዳጅ ግዢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣

ነጋዴዎች ደግሞ የግብይት ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ፍጥነታቸው እንዲጨምር ይረዳል።

ነዳጅ አቅራቢዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና አሽከርካሪዎች የባለራዕዮች ባንክ የሆነውን ቡና ባንክ በመጠቀም የነዳጅ ግብይትዎን ይፈጽሙ  ሲል ቡና ባንክ ለቁም ነገር ሚዲያ በላከው መግለጫ  ተመለክተናል !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe