ብሔራዊ ባንክ ያፀደቀው የሲንቄ ባንክ የፕሬዚዳንትነት ሹመት ውዝግብ አስነሳ 

 ብሔራዊ ባንክ ያፀደቀው የሲንቄ ባንክ የፕሬዚዳንትነት ሹመት ውዝግብ አስነሳ ባንኩ በበኩሉ ግራ ተጋብቻለሁ ብሏል፤

 በቅርቡ ከማይክሮ ፋይናንስነት ወደ ባንክነት ያደገው ሲንቄ ባንክ  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ  የፀደቀው  የፕሬዝደንቱ ሹመት በልዩ ሁኔታ በሚል የሰጠው ይሁንታ ጥያቄ አስነሳ፡፡  ሲንቄ ባንክ በበኩሉ ብሔራዊ ባንክ የፕሬዚዳንቱን ሹመት ‹ በልዩ ሁኔታ› ብሎ መፍቀዱ  ግራ እንዳጋባው  ጠቅሶ ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑን የጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

  ከሰሞኑ ብሔራዊ ባንክ  ለሲንቄ ባንክ የፕሬዝደንትነት ሹመት  ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው የይሁንታ ምላሽ ደብዳቤ ላይ  የአቶ ንዋይ መገርሳን ሹመት በልዩ ሁኔታ መፍቀዱን አስታውቋል፡፡    ይህ ብሔራዊ ባንክ  ውሳኔ በዘርፉ ያሉትን ባለሞያዎች ግራ ያጋባ ከመሆኑም በላይ በሕጉ መሠረት ከተቀመጠው አሰራር ያፈነገጠ ስለመሆኑ ተስተውሏል፡፡“ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ  ሁሉንም ባንክ በእኩልንት በሕግ መሰረት ማስተናገድ  ሲገባው ለምን በልዩ ሁኔታ ሲል መፍቀድ እንደፈለገ የፋይናንስ ባለሙያዎች ተችተዋል፡፡

 የሲንቄ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ንዋይ መገርሳ የብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ ግራ እንዳጋባቸው ገልፀው ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ የተጠየቀው በህጉ መሰረት ይሁንታ እንዲሰጥ ወይም እንዲከለክል እንጂ ለምን በልዩ ሁኔታ ፈቅጃለሁ እንዳለ እኔም ግራ ገብቶኛል ማላታቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል፡፡  በማከልም በብሔራዊ ባንክ  መመሪያ መሰረት በፕሬዝደንትነት ለመስራት የሚያበቃ በቂ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ አለኝ ያሉት አቶ ንዋይ ለጉዳዩ ማብራሪያ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከኢብባ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe