ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን የገለፀው ትምህርት ሚኒስትር መምህራን “በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስችል የመምህራን ባንክ” የማቋቋም ሀሳብ እንዳለዉ ፍንጭ ሰጥቷል።
ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ( ፕ/ር) እንደተናገሩት ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆኑ ይህንን ለማስተካከል ” ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ስርዓቶች ይዘረጋሉ” ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባም አስረድተዋል ።
ይህ የተባለዉ የትምህርት ሚኒስቴርን የበጀት ዓመቱ የ3 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ በሚመለከት ከሚመለከተዉ አካል ጋር ዉይይት ባደረገበት ወቀት ነዉ።
(Capital)

