ቻይና በአሜሪካ የተጣለባትን የታሪፍ መጠን ያካክሳል ያለችዉን የ15 በመቶ ታሪፍ አሜሪካ ላይ እንደምትጥል አስታወቀች፡፡
ቻይና ከአሜሪካ በሚገቡ የከሰል እና በተጣራ የተፈጥሮ ጋዝ ላይ የ15 በመቶ ጭማሪ እንደምታደርግ አስታወቃለች፡፡
ጭማሪዉ አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የአስር በመቶ ጭማሪ ማድረጓን ተከትሎ ሲሆን ቻይናም የ 15 በመቶዉ ታሪፍ እንደምትጥለረ እወቁት ነው ያለችዉ፡፡
የቻይና የገንዘብ ሚኒስትር በዛሬዉ እለት እንዳስታወቁትም ከሚጣለዉ ታሪፍ ሌላ ከአሜሪካ በሚገቡ ድፍድፍ ነዳጅ፤የግብርና መሳሪያዎች፤የከባድ ተሸከርካሪ እና ፒካፕ መኪናዎች ላይም የአስር በመቶ ጭማሪ ይደረጋል ብለዋል ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አዲሱ ጭማሬ አሜሪካ በራሷ ፍላጎት ያመጣችዉ ያሉ ሲሆን ፤የአለም የንግድ ድርጅት ህግንም ጥሳለች፤ይህንም ችግር የራሷ በመሆኑ ማንም ሊፈታዉ አይችልም የነበረንን መደበኛ የንግድ ግብይት እና ትብብራችንን አሜሪካ አፍርሳዋለች ብለዋል፡፡
የታሪፍ ጭማሪዉ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ቻይና ከ አሜሪካ ጋር ማንኛዉንም ንግግሮችን ለማድረግ በሬ ክፍት ነዉ ብላለች፡፡
ልኡል ወልዴ

