ቻይና እና ፓኪስታን የኢራንን ጦርነት ለማስቆም ባለ 5 ነጥብ የሰላም እቅድ አቀረቡ

አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ከአንድ ወር በላይ መሻገሩን ተከትሎ ቻይና እና ፓኪስታን ግጭቱን በአስቸኳይ ለመግታት የሚያስችል ባለ 5 ነጥብ የሰላም ስምምነት ዕቅድ ይፋ አድርገዋል፡፡

የቀረበው የሰላም ሰነድ በዋናነት አፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት በሚለው ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነም ተዘግቧል፡፡ይህ የሰላም እቅድ የተዘጋጀው የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ቤጂንግ ተጉዘው ከቻይና ባለስልጣናት ጋር ከመከሩ በኋላ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥረቱን ሰላምን ለማስፈን የሚደረግ አዲስ ጅምር ሲል ገልጾታል፡፡ቻይና እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያሳየችው አቋም የተቀዛቀዘ ነው ቢባልም አሁን ግን ጥረቷን ለማጠናከር እየሞከረች ነው ተብሏል፡፡

ቻይና ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያላት ስትሆን ከሌሎች የእስያ ሀገራት በተለየ ለከፋ የነዳጅ እጥረት አልተጋለጠችም፡፡ ይሁን እንጂ ቀውሱ ምንም መረጋጋት ሳያሳይ የሚዘልቅ ከሆነ ግን በኢንደስትሪዎቿ ላይ ከፍተኛ ተዕጽኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው፡፡

ይህንን ከግምት በማስገባትም የቻይና መንግስት ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ተብሏል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe