ቻይና የእጅ መዳፍን ስካን በማድረግ የክፍያ ቴክኖሎጂን አስተዋወቀች!

📌 ኤቲኤም ካርድም ሆነ ስልክ አያስፈልግም

ቻይና ኤቲኤም ካርዶችም ሆነ ስልኮች ሳያስፈልጉ የእጅ መዳፍን ስካን በማድረግ ብቻ ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጋለች፡፡

ይህም ማለት ማንኛውም መደብር ወይም ሱቅ ገብቶ ግብይት ለመፈጸም የሚያስፈልገው እጅ ብቻ ነው – የእጅ መዳፍ!

አዲሱ የክፍያ ቴክኖሎጂው፤ በቴንሴንትስ ዌይክሲን ፓልም ስካን እና አሊፔይ ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ የበለጸገ ሲሆን፤ ቴክኖሎጂው የመዳፍን ውጫዊ ቅርጾችና የደም ስሮችን በፍጹም ልከኝነት ያነባል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በWeChat Pay ወይም Alipay ይከናወን የነበረው የክፍያ ሥርዓት፣ አሁን በቀላሉ እጅን ስካነር ላይ በማድረግ ብቻ በቅጽበት መፈጸም ይቻላል – በአዲሱ የቻይና የክፍያ ሥርዓት፡፡

በሺዎች በሚቆጠሩ 7-ኢለቨን መደብሮች፣ የሜትሮ ጣቢያዎች፣ አየር ማረፊያዎችና ካምፓሶች ውስጥ የገባው አዲሱ ቴክኖሎጂ፤ በቅርቡ በዓለም ዙሪያ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል፡፡

ቴክኖሎጂው ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ ነው ተብሏል፡፡ ነገር ግን የባዮሜትሪክ መረጃ አንዴ ከተጣሰ ሊቀየር ስለማይችል የግል ምስጢሮች ደህንነት ላይ ስጋቶች መፍጠሩ አልቀረም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe