አላስፈላጊ የቆዳ ፀጉር ማስወገድ

የሰውነታችን በጠፈጥሮ ከውስጥ እግራችንና ከእጃችን መዳፍ ውጭ በሙሉ በፀጉር የተሸፈነ ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን በጣም ወፍራም ፀጉርና ጎልቶ የሚታይ ሲሆን የሌሎች ደግሞ እጅግ በጣም ስስ በቀላሉ በአይን ለማየት የሚያዳግት ይሆናል፡፡ በሴቶች ገላ ላይ ፀጉር መብቀሉ የተለመደ ቢሆንም የፋሽኑ ዓለምና የባህል ተጽኖ ይኸው ፀጉር እንዲወገድ ምክንያቶች ይሆናሉ፡፡ በተለይም በሴቶች እግር ፣ እጅ ፣ብብት ላይ ያሉ ፀጉሮች እነዚህን አካሎች የሚያሳይ ክፍት ልብስ በሚጠቀሙበት ወቅት ጥርት ያለና ለስላሳ ቆዳ ስለማይኖራቸው ውበትን ይቀንሳል፡፡ ከአይን በላይ የሚገኘው የቅንድባችን ፀጉር ደግሞ ከመጠን በላይ የበዛ ከሆነና የተስተካከለ ቅርጽ ከሌለው ለዕይታ አይማርክም፡፡ ለዚህ እንደትልቅ መፍትሔ ተደርጎ የሚወሰደው ይህን አላስፈላጊ ፀጉር በተለያዩ ዘመናዊ መንገዶች ማስወገድ ነው፡፡
መላጨት(shaving)
መላጨት ወይም (shaving) ፀጉርን ከቆዳችን ላይ ምላጭን በመጠቀም የምናነሳበት መንገድ ሲሆን በተለይም ጠቀሜታው ለእግርና ብብት አካባቢ የሰውነት ክፍሎች ነው፡፡ ፀጉርን መላጨት ጥሩ የሆነው ጎኑ ስለቱ እንዳይቆርጠን ተጠንቅቀን ከጠጠቀምን ፈጣንና ምንም አይነት ህመም የሌለው ሲሆን፤ መጥፎ ጎኑ ደግሞ የተላጨው ፀጉር በትንሽ ቀናት ውስጥ ተመለልሶ ይበቅላል፡፡ አልፎ አልፎም በአንዳንዶች ላይ ከፍተኛ ሽፍታ እና የቆዳ መሻከር ይፈጠራል፡፡ ሰውነትሽ ላይ ያለውን ፀጉር በመላጨት ማስወገድ ከመረጥሽ በመጀመሪያ ውሃንና አረፋን የቆዳሽ ፀጉር ላይ በሚገባ ቀቢ፡፡ በመቀጠልም መላጨት ከመጀመርሽ በፊት የተጠቀምሽው አረፋው ወይም የጄሉ ክሬም ፀጉሩን በሚገባ እንዲያነሳው ቆዳሽ እስኪርስ ለተወሰነ ደቂቃዎች አቆይው ፡፡ በቀጠል የፀጉርሽን አቅጣጫ በመከተል መላጨት ትችያለሽ፡፡
ፀጉርን በመላጥ ማንሳት (waxing)
ይህ ዘዴ ፀጉርን ሙሉ ለሙሉ ከቆዳ ሥር ነቅሎ ለመጣል የሚጠቅም ነው፡፡ ቆዳሽን በመጀመሪያ ዋክስ ከቀባሽ በኋላ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀን ጨርቅ ዋክስ በተቀባው ቆዳ ላይ መለጠፍ፡፡ በመቀጠልም የጨርቁን ጫፍ ይዞ መላጥ፡፡ ወይንም ደግሞ መጀመሪያውኑ ዋክስ አካቶ የያዘ ጨርቅ በመጠቀም በሰውነትሽ ላይ ያለውን አላስፈላጊ ፀጉር ማስወገድ ትችያለሽ፡፡ ዋክስን መጠቀምሽ መልካም ጎኑ ከ2 – 6 ላሉ ሳምንታት በሰውነትሽ ላይ አላስፈላጊ የሆኑ ፀጉሮች አይበቅሉም፡፡ መጥፎ ጎኑ ደግሞ በዋክስ ፀጉርን በምታስወግጂበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ህመም አለው፡፡ አልፎ አልፎም የቆዳ መበለዝ ሊያጋጥምሽ ይችላል፡፡ ሌላው ደግሞ ማወቅ ያለብሽ ምናልባትም በዋክስ ከተወገዱት ፀጉሮች መካከል አንዳንዶቹ ደግመው አይበቅሉም፡፡ በዋክስ ፀጉርን በምታስወግጂበት ወቅት ፀጉርሽ ለዚሁ ተግባር ምቹ እንዲሆን በሚገባ ማደግ ስለሚኖርበት እስኪያድግ ድረስ በትግስት መጠበቅ ይኖርብሻል፡፡ ፀጉሩን በዋክስ ካስወገድሽ በኋላ ደግሞ ሽፍታንና የቆዳ ከለር መለወጥን ለመከላከል እንዲረዳሽ ባክቴሪያን የሚያጠፉ ክሬሞች መቀባት ይኖርብሻል፡፡ ነገር ግን ተቆጥቶና ቀልቶ የሚታይ ቆዳ ካለሽ ዋክስ ለመጠቀም በፍጹም እንዳትሞክሪ፡፡
ፀጉርንለመነቃቀል የሚረዱ ክሬሞች (depilatory creams)
እነዚህ ክሬሞች ፀጉር በቆዳ ላይ እንዳለ በማንሳት ሙልጭ ብሎ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ክሬሙን ከተቀባሽ በኋላ ከ5 – 10 ደቂቃዎች ብቻ በማቆየት ታጠቢው ፡፡ ነገር ግን ማስተዋል ያለብሽ ነገር የእያንዳንዱ ምርት ይዘት ስለሚለያይ በምርቱ ላይ የተፃፉትን የአጠቃቀም መመሪያወች በደንብ ማንበብ ይኖርብሻል፡፡ አላስፈላጊ ፀጉርን ማስወገጃ ክሬሞችን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለተለያዮ የሰውነት ክፍሎችም የተለያዩ ክሬሞች የሚመረቱ መሆኑን ልትገነዘቢ ይገባል፡፡ በክሬም ፀጉርን ማስወገድ መልካም ጎኑ የምርቱ ርካሽ መሆንና ውጤቱም በምላጭ ከምትላጪው የበለጠ እስከ አንድ ሳምንት ሊቆይልሽ ይችላል፡፡ በተቃራኒው ጥሩ ያልሆነው ጎኑ ደግሞ ፀጉርን ለማስወገድ ጊዜ ይወስዳል ፣ ቆዳን ያጨማልቃል፣የተወሰኑት ምርቶች ሽታቸው ጥሩ አይደለም፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe