የሆሊውድ ፊልሞች ፈርጥ ቻክ ኖሪስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
ታዋቂው አሜሪካዊ የሆሊውድ ፊልሞች ተዋናይ እና የማርሻል አርቲስት ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
በፈረንጆቹ 1940 በኦክላሃማ የተወለደው ኖሪስ በማርሻል አርት ከመታወቁ በፊት በአሜሪካ አየር ኃይል አገለግሏል፡፡
በአክሽን ፊልሞቹ የሚታወቀው ኖሪስ ዎከር እና ቴክሳስ ሬንጀር በተሰኙ ተከታታይ ፊልም በልዩነት እንዲሁም በወጣቶች ዘንድ ፎሬቨር ሞርታላይዝድ በሚለው ፊልሙ ይታወቃል፡፡
ባገጠመው ህመም በሃዋይ የህክምና ክትትል ሲደረግለት የቆየው ቻክ ኖሪስ÷ በተወለደ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

