አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ ሎራን ኮል የተባለው አሜሪካዊ የ57 ዓመት እድሜ ያለው ሲሆን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ ወንጀለኛ የሞት ፍርድ የተላለፈበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ታስሮ በነበረበት ፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ገዳይ መርዝ በመርፌ ከተወጋ በኋላ ህይወቱ አልፏል። ግለሰቡ የገዛ እህቱን በመድፈር ወንጀል ከተመሰረተበት ክስ በተጨማሪም የፍሎሪዳ ዩንቨርሲቲ የሆነ የ18 ዓመት ወጣት ግድያም ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
አሜሪካ የተያዘው 2024 ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ 13 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ የፈጸመች ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የሞት ፍርድ በብዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ከፍተኛዋ አድርጓታል፡፡ አሜሪካ ካሏትግዛቶች ውስጥ 23ቱ የሞት ፍርድን የሚፈጽሙ ሲሆን ቀሪዎቹ 7 ግዛቶች ደግሞ የሞት ፍርዶችን ወደ እድሜ ልክ እስር ይቀይራሉ፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ፖፑሌሽን ሪቪው ጥናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡ ከአሜሪካ በተጨማሪም ጥብቅ ህግ ያላቸው ሀገራት ፦
– ሳውዲ አረቢያ፣ – ቻይና፣- ደቡብ ኮሪያ፣- ቸክ ሪፐብሊክ፣- ሰሜን ኮሪያ እና ፓኪስታን ዋነኞቹ ናቸው።
መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።

