አሜሪካ እና ኢራን የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በአሸማጋዮች በኩል እየተደራደሩ ነው ተባለ

አሜሪካ እና ኢራን በቀጣይ ሊከሰት የሚችለውን ከፍተኛ ግጭት ለማስቀረት ለ45 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በአደራዳሪዎች በኩል ንግግር ላይ መሆናቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ዋሽንግተን እና ቴህራን በቀጠናው አሸማጋዮች አማካኝነት የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስና ተጨማሪ ውጥረቶችን ለማስቀረት እየጣሩ መሆናቸውን አክሲዮስ ጽፏል፡፡

አስታራዊ ወገኖች በዋናነት የሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦች እንቅስቃሴ እና በኢራን የዩራኒየም ክምችት ዙሪያ ትኩረት አድርገው እየመከሩ ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለአክሲዮስ የዜና ምንጭ እንደገለጹት ድርድሮች ይሳካሉ የሚል እምነት እንዳለቸው ነው፡፡ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጥሩ እድል ያለ ይመስለኛል፤ነገር ግን ኢራን ይህንን ለማድረግ ካልወሰነች ሁሉንም ነገር አጋየዋለሁ በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ድርድር እያመቻቹ ያሉት ፓኪስታን፡ግብጽ እና ቱርክ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቀጥታ መልዕክቶችም በልዩ መልዕክተኛው እስቲቭ ዊትኮቭ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ በኩል እንዳለ ታውቋል፡፡

ከቀረበው ምክረ ሀሳብ መካከልም ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም እንዲረዳ የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት መድረስ የሚለው ይገኝበታል፡፡

አሸማጋዮች የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም መከፈትና በከፍተኛ መጠን በልጽጎ የሚገኘው የዩራኒም ጉዳይ የመጨረሻው ስምምነት ላይ የሚያደርሱ መንገዶች ናቸው ብለዋል፡፡

ኢራናዊያን ሊደረስ የሚችለው ስምምነት እንደ ጋዛው ወይም እንደ ሊባኖሱ አይነት በወረቀት ላይ ብቻ እንደሰፈረው መሆን የለበትም የሚል ግልጽ አቋም ይዘዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ወሽመጥ ምንም ቢሆን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረው ሁኔታው አይመለስም ሲል አቋሙን አስታውቋል፡፡

አሸማጋዮች ለኢራናዊያን ባለስልጣናት አሁን ስዓት የለንም፤ተጨማሪ ጥፋት ከመድረሱ በፊት አንድ ነገር ማድረግ ይኖርባናል ብለዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe