አምስት አትሌቶች ከአበረታች እጽ ጋር በተገናኘ አስተዳደራዊ ቅጣት ተጣለባቸው

አምስት ጸረ-አበረታች ቅመሞችን የተጠቀሙ አትሌቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

በ2017 የጸረ አበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት የፈጸሙ አምስት አትሌቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጽያ ጸረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ምርመራ ከተደረገባቸው 1ሺ196 አትሌቶች ሦስቱ አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው በመገኘታቸው ከሁለት እስከ ሰባት ዓመት ድረስ በማንኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንይካፈሉ መታገዳቸውን ባለስልጣኑ ገልጻል፡፡

ሌሎች ሁለት አትሌቶችም ናሙና ለመስጠትና የአድራሻ ምዝገባ ለማድረግ ተባባሪ ባለመሆናቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ በሚጀመረው 20ኛው የቶኪዮ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተቀመጡ መስፈርቶችን ለማሟላት ለ143 አትሌቶች ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ማለፋቸው ተነግሯል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe