አስገዳጅ የባንኮች ውህደት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ገለፁ።
እንደ ገዥው ገለፃ ዋነኛ አላማው ችግር ያለባቸውን ባንኮች ለማዳን ነው።
በቅርቡ የፀደቀው የባንክ ስራ አዋጅ የባንኮችን ውህደት በተመለከተ የገለፀ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ እየተጠበቀ ነው።
ብሄርን መሰረት አድርገው ስለተመሰረቱ ባንኮች በውህደት ወቅት ስለ ሚያጋጥም ተግዳሮት የተጠየቂት አቶ ማሞ ውህደትን ጨምሮ አጠቃላይ የባንክ ስራ በህግ እንደሚመራ አስታውሰው፣ “ከዚህ አኳያ ከብሄር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ በተለይ በአስገዳጅነት የሚፈፀም ውህደት ላይ የሚኖረው ተፅእኖ አናሳ ነው፣” ብለዋል።
አስገዳጅ የባንኮች ውህደት እንደሚኖር ብሄራዊ ባንክ ገለፀ!!

