በለንደን ማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳደረው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች መግባት የቻለ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል። በታሪኩ በማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳዳረው ዮሚፍ ቀጀልቻ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የገባበት 1 ሰዓት 59.41 ደቂቃ የኢትዮጵያ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ የገባበት ሰዓት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኗል።
የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊው ሰባስቲያን ሳዌ 1 ሰዓት 59.30 ደቂቃ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ሆኗል። የ30 ዓመቱ አትሌት ከሦስት ዓመት በፊት በሀገሩ ልጅ ኬልቪን ኪፕቱም ተይዞ የነበረውን የ2 ሰዓት 00.35 ደቂቃ ክብረ ወሰን በመስበር አዲስ ታሪክ ሠርቷል።

