አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የሪቨር ፕሌት ስታዲየም በሆነው የክብር አቀባበል ተደረገለት

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበው ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ከአስደናቂው ድሉ በኋላ ሌላ የማይረሳ አጋጣሚ አስተናግዷል። የደቡብ አሜሪካው ኃያል ክለብ ሪቨር ፕሌት፣ ኢትዮጵያዊውን ጀግና በግዙፉ ስታዲየሙ ኤል ሞኑመንታል የክብር አቀባበል አድርጎለታል። ዮሚፍ ስታዲየም በደረሰበት ወቅት በደጋፊዎችና በክለቡ አመራሮች ከፍተኛ የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።

በሥነ ሥርዓቱም ላይ የሪቨር ፕሌት ክለብ ተወካዮች የዮሚፍን ስም እና ልዩ ስኬቱን የሚያጎላ የክለቡን ማሊያ በስጦታ አበርክተውለታል።

Sourceኢቲቪ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe