አዲስ አበባ  በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ 15 ከተሞች ቀዳሚውን ደረጃ እንደያዘች አንድ ጥናት አመለከተ፤

በየዕለቱ ከክልል ከተሞች ወደ ከተማዋ በሚገባው ህዝብ ሳቢያ ለከፍተኛ የኑሮ ውድነት የተጋለጠችው አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን ከኑሮ ውድነት መታደግ ያቃታት ይመስልላል፡፡

ሰሞኑን በዚሁ ዙሪያ ጥናት ያደረገው ቢዝነስ ኢንሳይደር የተባለ ድረ ገጽ አዲስ አበባ ከተማ  በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ 15 ከተሞች ቀዳሚውን ደረጃ እንደያዘች ዘግቧል።

በአዲስ አበባ የፍጆታ ሸቀጦች ዋጋ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ከተሞች ጋር ሲነጻጸር በጣም ውድ ሆኖ እንደተገኘ በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡንን ዘገባው ገልጧል።

ጥናቱ አራት የደቡብ አፍሪካ ከተሞችን በኑሮ ውድነት ከ15ቱ ውስጥ ሲያካትት በተመሳሳይ አራት  የሞሮኮ ከተሞችም ተመሳሳይ ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል፤

የከተሞች የኑሮ ውድነት ደረጃ የተነጻጸረው፣ የምግብ፣ ለአልባሳት እና የጤና ወጭዎችን በመስፈርትነት በመውሰድ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከፍተኛው 58.92 ነጥብ ተሰጥቷታል። በንጽጽሩ ናየመሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ ውድነት ላይ ያተኮረ ሲሆን እንደ መኖሪያ ቤት ዋጋና ኪራይ በጥናቱ አለመካተቱን ድረ ገፁ አስታውሷል፤

በዘገባው መሠረት አዲስ አበባ በኑሮ ውድነት ከ15ቱ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ስትሆን የናይጀሪያዋ አቢጃ እና የዚምባብዌ ዋና ከተማ ሀራሬ ሁለተኛና ሶስተኛ ውድ ከተሞች ሆነዋል፤

የደቡብ አፍሪካዎቹ  ጆሃንስበርግና  ፕሪቶሪያ አራተኛና አምስተኛ ሲሆኑ የቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቩሮኒ ስድስተኛ ሆናለች፤

የጋና ዋና ከተማ አክራ ሌላዋን የደቡብ አፍሪካ ከተማ  ኬፕታውንን ተከትላ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ስትመደብ የሞሮኮዋ ማራካሽ ዘጠነኛ ደረጃ  ላይ ተቀምጣለች፡፡

የናሚቢያዋ ዊንድሆክ የሞሮኮዋ ታንግርና የደቡብ አፍሪካዋ ደርባ ከ10 እስከ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ የሞሮኮዋ ካዛብላንካ የኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢና የሞሮኮዋ ዋና ከተማ ራባት የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች አግኝተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe