የኖ ሞር ወይም እምቢ! ንቅናቄን በመላው ዓለም ካቀጣጠሉትና በውጪ የሚኖረውን ዲያስፖራ ካንቀሳሱት ኢትዮጵያውያን መሀከል አንዷ የሆነችወው የጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ እናት ፕሬፌሰር ሐረገወይን አሰፋን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማካሪነት ሊቀጥራቸው መሆኑ ተሰማ፤
ፕሮፌሰር ሐረገወይን ወደ አሜሪካ ሄደው ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ይዘው በጥናትና ምርምር ዘርፍ ከመሰማራታቸው በፊት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፋርማሲ የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ማዕረግ በመመረቅ ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እጅ የወርቅ መዳሊያ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን ለዘጠን ዓመታት በዩኒቨርሲቲው ፋርማሲ ትምህርት ቤት ውስጥ በረዳት መምህርነት እና በተመራማሪነት አገልግለዋል፤
በቅርቡ የ1 ሚሊዮን ዲያስፖራን ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት ከጋዜጠኛ ሔርሜላ ጋር መጥተው የነበሩት ፕሮፌሰር ሐረገወይን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአብረን እንስራ ጥያቄ እንዳቀረበላቸው የዩኒቨርሲቲው ምንጮች ለአዋዜ ተናግረዋል፤
ፕሮፌሰር ሐረገወይን ከዩኒቨርሲቲው የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸው የታወቀ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው የሳይንስ ፋኩሊቲ በመድሃኒት ጥናትና ምርምር ዘርፍ እንዲሁም የሁለተኛና የሶስተና ዲግሪ ተማሪዎችን ያማክራሉ ተብሏል፤
ፕሮፌሰር ሐረገወይን በአሜሪካ ሀገር በመድሃኒት ዘርፍ ባደረጉት ምርምር በአዲስ የመድሃኒት ፖተንት የ2019 ሄሮ ኦፍ ኬሚስትሪ አዋርድ የተባለ ሽልማት ማግኘታቸው ተዘግቧል፤
ፕሮፌሰሯ ከ10 ሰዓት በላይ በምርምር ላብራቶሪ ውስጥ የመስራት የረዥም ዓመታት የምርምር ልምዳቸውን በመያዝ ኢትዮጵያውያን ጀማሪ የመድሃኒት ተራማሪዎችን ጥናት ያግዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፤