የጠቅላይ ሚኒስትሯን ጥያቄ በሚመለከት ግን እስካሁን ሰሜን ኮሪያ የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡
ላለፉት ከ20 ለሚበልጡ ዓመታት በጃፓን መሪዎች ያልተሳካውን ነገር አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ አስበዋል፡፡ ነገር ግን በ2024 የሰሜን ኮሪያው መሪ እህት ኪም ዮጁ ከጃፓን ጋር የሚደረግ ምንም አይነት ንግግር እንደማይኖር መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሳኒ ታካቺ ጃፓን ከአስር ዓመታት በፊት ዜጎቿ በሰሜን ኮሪያ ተጠልፈው ከተወሰዱባት ወዲህ መልካም ግንኙነት ከሰሜን ኮሪያ ጋር የላትም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በእሳቸው የስልጣን ዘመን ይህንን ክፍተት ለማስተካከል እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ቢያንስ 17 የሚደርሱ ጃፓማዊያን በ1970 እና 1980 ተጠልፈው ወደ ሰሜን ኮሪያ ተወስደዋል፡፡ በ2002 አምስቱ መመለሳቸው ተነግሯል፡፡ ከዚያን ወዲህ ግን ምንም አይነት ውጤት አልታየም፡፡
ጃፓን እና ሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የላቸውም በተጨማሪም ፒዮንግ ያንግ የተጠለፉት ጃፓናዊያን ጉዳይ ተፈቶ አልቋል ብላ ታምናለች፡፡//

