ኢራናዊያን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛቻ የሚሸበሩ አይደሉም ሲሉ ጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ካሚኒ ገለጹ

ኢራናን ፕሬዝዳንት በዋሽንግተን የሚደረግ ጥቃት ቀጠናውን ወደ ጦርነት ያስገባዋልም በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ጦርነትንም ሆነ ድርድር እንደማስፈራሪያ ለመጠቀም እየሞከረ ነው ኢራናዊያን ግን ለእንደዚህ አይነቱ ማስፈራሪያ የሚንበረከኩ ህዝቦች አይደሉም ብለዋል፡፡

እኛ የትኛውንም ሀገር የማጥቃት ፍላጎቱ የለንም ነገር ግን ለሚቃጣብን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ በዚህ ስዓት ጦርነቱን በእኛ ላይ ከከፈተችውም ጦርነቱ ቀጠናዊ እንደሚሆን ይታወቅ ሲሉ የኢራን ሁለንተናዊ መሪው አስታውቀዋል፡፡

ነገሮች በዚህ መልክ ተካረው በሚገኙበት በዚህ ስዓት በሌላ በኩል ዲፕሎማሲዊ ጥረቶች እንደቀጠሉ መሆናቸውም እየተነሳ ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ንግግር ማድረግ እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

ቴህራን በበኩሏ ከአሜሪካ ጋር ሀቀኛ በሆነ መንገድ ብቻ ለንግግር እንደምትቀመጥ ገልጻ፤ስጋት ባለበት ሁኔታ ግን ለንግግር ዝግጁ እንደማትሆን እያነሳች ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወታደራዊ እርምጃ በኢራን ለመውሰድ እንዲያስቡ ካደረጓቸው ነጥቦች መካከል ለሦስት ሳምንት ገደማ ሲደረግ የቆየውና አሁን ለጊዜውም ቢሆን የረገበው በኢራን ውስጥ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ እና በኒውክሌር ፕሮግራሟ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ትራምፕ ወታደራዊ አማራጩ በጠረጼዛው ላይ እንዳለ በመግለጽ እያስጠነቀቁ ባለበት ስዓት ነው አያቶላህ አሊ ካሚኒ የትኛውም ወታደራዊ እርምጃ ቀጠናውን ወደለየለት ጦርነት ይከተዋል ሲሉ ያሳሰቡት፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ከCNN ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢራን ጦርነቱን ለማስቀረት ለጦርነቱ እየተዘጋጀች ነው ብለዋል፡፡ ይህን ስንል ግን እኛ ኢራናዊያን ጦርነቱን እንፈልገዋለን ማለታችን ሳይሆን ጦርነቱን ለማስቀረት ነው መዘጋጀቱ ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሀሰትን መሠረት ያደረጉ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች እና የተወሰኑ አካላት ፕሬዝዳንት ትራምፕን ወደ ጦርነቱ ጎትተው ለማስገባት እንደሚፈልጉ እናውቃለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

እነዚህ አካላት ትራምፕን ወደ ጦርነቱ ማስገባት የሚፈልጉት የራሳቸውን ጥቅም በማስላት ነው፤ፕሬዝዳንት ትራምፕ የእራሳቸውን ትክክለኛ ውሳኔ ግን ይወስናሉ ብዬ አስባለሁ ብለዋል፡፡

በተሳሳተ ስሌት ምክንያት ሊፈጠር ይችላል ተብሎ የሚሰጋውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ለማስቀረት ዋነኛው ጉዳይ የቀጥታ ንግግር ማድረግ ነውና በዚህ እረገድ ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ ለመገናኘት ምን አስባችኋል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሚያሳዝን ሁኔታ እኛ በአሜሪካ ላይ እምነት የለንም ብለዋል፡፡

ትርጉም ያለውን ድርድር ለማካሄድ መተማመን ትልቁ መሠረት ነው እኛ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ባደረግናቸው ንግግሮች ይህን የሚያሳይ አንድም ድርድር አላየንም ብለዋል፡፡

በ2015 በነበረው ድርድርም ሆነ ባለፈው ዓመት በሰኔው የጦርነት ወቅት ይህንን ነው የተረዳነው በማለት ተናግረዋል፡፡ እናም ትክክለኛ ድርድር ከአሜሪካ ጋር ለማድረግ በመካከላችን የነገሰውን አለመተማመን በቅድሚያ ማስወገድ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ይህንን እምነት ለመመለስም የቀጠናው ወዳጅ የሆኑ ሀገራት ምንም እንኳን ጉዳዩ ቀላል ባይሆንም ጥረት ላይ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያን መታጠቅ የለባትም በዚህ ከተስማማች  ድርድሩ ይሰምራል የሚል ልጥፍ አጋርተዋል ጉዳዩ እሱ ብቻ ከሆነ ከስምመነት ላይ ለመድረስ ቀላል ይመስለኛል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለሰላማዊ አገልግሎት እንጂ የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ እንደማታውለው በመግለጽ ትታወቃለች፡፡

እናም በዚህ ረገድ ኢራን መቼም ቢሆን ኒውክሌርን ከሰላማዊ አገልግሎት ወጪ አናውለውም ብለዋል፡፡ ድርድሩ ላይሰምር የሚችለው በማንስማማባቸው ነጥቦች ላይ ብቻ አይናችንን ከጣልን ነው ብለዋል፡፡

የማንስማማባቸው ካሏቸው ነጥቦች ውስጥም የባላስቲክ ሚሳኤሎቿ ጉዳይ እና በቀጠናው ስላሉት የውክልና ተዋጊዎቿ ነው፡፡

ነገሮች ተካረው ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ለሁሉም ወገን እጅግ አስከፊ ይሆናል የሚል ምልከታ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል፡፡

ጦራችን ካለፈው የሰኔው ጦርነት በበለጠ ሁኔታ መዘጋጀቱን እንዲሁም ሚሳኤሎቻቸውም በተመሳሳይ በዚያው ጦርነት ሙከራ ማደረጋቸውን በማንሳት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ተናግረዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe