ኢራን በአባልነት ያለችበትና 57 የእስላም አገራት ትብብር የሆነው ጥምረት የእስራኤል ካባኔ ያጸደቀውን ውሳኔ ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲቀመጡ በደብዳቤ ጠይቃለች።
ኢራን እና ግብፅ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ልታከናውን ባቀደችው ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ መልስ ለመስጠት የእስላም አገራት በጋሪ እንዲቆሙ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ አገራት እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ነው ላሉት የዘር ማጥፋት ተግባርና በሊባኖስ ትፈጽመዋለች ላሉት ጥቃት የጋራ መልስ ለመስጠት በአንድነት መቆም አለብን ብለዋል። ኢራንና ግብፅ 57 ሙስሊም በብዛት ያለባቸው አገራት ወደ ጋዛ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ ማድረግና ሌሎች የመፍትሔ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው ብለው ያምናሉ።
በሊባኖስም ቢሆን እስራኤል ከደቡባዊ ሊባኖስ ለቃ መውጣት እንዳለባት ገልጸዋል። የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒ የጋዛን ከተማ ይዞ ለሚደረገው አዲስ የእስራኤል ዘመቻ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል። ኢራን ይህንን ማድረግ እንዲቻል ነው የትብብር አባል አገራትን ስብሰባ እንዲቀመጡ የጠየቀችው። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ይህን የሚጠይቅ ደብዳቤ ለሳውዲና ለቱርክ ልከዋል።
ኢራን 57 የሙስሊም ሀገራት ያሉበትን ጥምረት አስተባብራ በእስራኤል ላይ ጦርነት የመክፈት ፍላጎት አላት የሚሉ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። የእስራኤል ካቢኔ በጋዛ ሰርጥ አዲስ ሙሉ ዘመቻ እንዲደረግ የሚጠይቀውን እቅድ ማጽደቁን ተከትሎ ኢራን ይህን ልታደርግ ትችላለች የሚል መላ ምት እየተሰራጨ ነው።
ኢራን እነዚህን ሙስሊም አገራት አስተባብራ በእስራኤል ላይ ጦር እንዲሰበቅ ማድረግ ትችላለች ወይ ካልን አይቻልም ነው መልሳችን ይላሉ የፖልቲካ ተንታኞቸ ። የዚህ ጥምረት አባል የሆኑት አገራት የተለያየ የፖለቲካ ስርዓት እና የውጭ ፖሊሲ የሚከተሉ ናቸው። አብዛኛዎቹ አገራት ደግሞ ከአሜሪካ:ከአውሮፓና ከራሷ ከእስራኤልም ጭምር ግንኙነት ያላቸው ናቸው። ስለዚህ በጋራ ጥምረት በእስራኤል ላይ ወታደራዊ እርምጃ ሊወስዱበት የሚችል እድል አይኖርም ነው የተባለው።
ኢራንና ግብፅ የጋዛ ሰርጥን ከአዲሱ የእስራኤል ሙሉ ዘመቻ ለመከላከል የእስላም አገራት በአንድ እንዲቆሙ ጠየቁ

