ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች

በማዕከላዊ ኢራን ” ዝድ ክልል “አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ ” በጥንቆላ ይተዳደራል ” የተባለ ሲሆን ወደሱ የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ ተደርጓል።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

መረጃው የአን አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe