ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል በጦርነቱ ከተገደሉብኝ ዜጎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ሲቪሊያን ናቸው አለች፡፡
ኢራን እስካሁን በጦርነቱ 3ሺ468 ዜጎቸ ተገድለዋል ያለች ሲሆን፤ከእነዚህም ውስጥ ወደ 1ሺ460 የሚሆኑት ሲቪሎች መሆናቸውን አስታውቃለች፡፡
በዚሁ ጦርነት ወታደራዊ ይዞታዎች ብቻ ሳይሆኑ የጤና ተቋማት፡ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችም የጥቃት ኢላማ ተደርገውብኛል ስትል ገልጻለች፡፡
እንደ አብነትም በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ውስጥ በሚናብ ከተማ በትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ወደ 170 የሚደርሱ ተማሪዎችና መምህራን መገደላቸው ይታወሳል ሲል ቴህራን ታይምስ ጽፏል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን የኢራንን ወታደራዊ አቅም ለማዳካም እና የኢራን ህዝብን ለመደገፍ የተደረገ አስፈላጊ እርምጃ ነው ብለውት የነበረ ቢሆንም የሆነው ግን እንዲህ ብሏል ዘገባው፡፡
የአሁኑ ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድሞ ትራፕም በኢራን ውስጥ የነበረውን ተቃውሞ በማበረታት እንዲሁም እርዳታም ጭምር እየመጣ ነው በማለት ድጋፍ ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ኤፕሪል 8 የተኩስ አቁም ስምምነት ከመደረሱ በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቴህራን ጥያቄዬን ካልተቀበለች ሙሉ ስልጣኔዋ በአንድ ምሽት እንዲያበቃ እናደርገዋለን በማለት ሲጽፉ መክረማቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
ከዚህ ባለፈ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝም ዋሽንግተን አረንጓዴ መብራቱን ካበራችላቸው ኢራንን ወደ ድንጋይ ዘመን ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር ሲልም ዘገባው አትቷል፡፡//

