ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን የማትከፍት ከሆነ እጅግ ከባድ የሆነ ምት ይጠብቃታል -ፕሬዝዳንት ትራምፕ

በዚህ ሳምንት መጨረሻም የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ በኩል ያለ ምንም እንቅፋት ማለፍ ይጀምራሉም ተብሏል፡፡ትራምፕ ዋሽንግተን እና ቴህራን ጥሩ ድርድር እያደረጉ ነው፤ነገር ግን ኢራን ንግግሩን የሚያውክ ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ ይኖርባታል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ለወራት ያህል የዘለቀውን ጦርነት ለማጠናቀቅ ፍላጎት እንዳላትም አንስተዋል፡፡

ትራምፕ አክለውም የሆርሞዝ ሰርጥ በጣም በቅርቡ ዳግም ክፍት ይሆናል፤ከኢራን ጋር የሚደረገውም ድርድር ቀጥሏል ሲሉ አሁን ያለውን ነባራዊ ሀቅ ገልጸዋል፡፡

ቴህራን በዚህ ስዓት እየተደረገ ባለው ድርድር ላይ ከስምምነት የማትደርስ ከሆን ግን የዋሽንግተን ብርቱ ክንድ ያርፍባታል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ትላትና አሁን ለኢራን የተሰጠው ዕድል የመጨረሻ እንደሆነ አንስተው፤ኢራንም ይህንን እድሏን እንዳታባክነው በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡

ትላንት ማክሰኞ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል ሆርሙዝ በጣም በቅርቡ ክፍት ይሆናል ወይ ደግሞ እጅግ ከባድ የተባለ ጥቃት በኢራን ላይ ሲያርፍ እንመለከታለን በማለት በቀጣይ የታሰበውን በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ሴንትኮም በበኩሉ በሆርሙዝ ሰርጥ ደቡባዊ ክፍል ባለው ዓለም አቀፍ የውሃ መስመር በኩል ለማለፍ ለሚፈልጉ የንግድ መርከቦች ሁሉ ነጻ እና ክፍት ነው ሲል አውጇል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሁን እየተደረገ ነው ያሉት ንግግር ከመጀመሩ አስቀድሞ ኢራንን ለመምታት ከጫፍ ድርሰው እንደነበርና በኢራን ተማጽኖ የመጨረሻ እድል እንደሰጡም ገልጸዋል፡፡ በርግጥ ትራምፕ ይህንን ቢሉም ኢራን ግን ከአሜሪካ ጋር ወደ ንግግር እንመለስ ብዬ ደጅ አልጠናሁም ብላለች፡፡ እናም በዚህ ስዓት ከአሜሪካ ጋር ድርድር ውስጥ አይደሉም ይልቁንስ ከኦማን ጋር በሆርሙዝ ዙሪያ እየተነጋገርኩ ነው እያለች ነው፡፡

እንዲህ ብለው ባይለምኙኝ ኖሮ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት ነበር የሚፈጸምባቸው ብለዋል፡፡ እንዲህ በምልጃና በልመና በጀመሩት ንግግር ላይ ከስምምነት ላለመድረስ ከወሰኑ የሚደርስባቸውን እነርሱም ቢሆን ጠንቅቀው ይረዱታል፤እኛም ምህረት የለሽ እርምጃ ነው የምንወስደው በማለት ዝተዋል፡፡ ኢራን መቼም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አትታጠቅም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ወዳጃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁም እኔ በስልጣን እያለሁ ኢራን ይህን መሳሪያ በፍጹም በእጇ እንደማታስገባው ማረጋገጥ እወዳለሁ ሲሉም በብዙ ንግግሮቻቸው ተደምጠዋል፡፡

ሳወዲ አረቢያም ብትሆን ኢራን የኒውክሌር ጦር ከታጠቀች እኔም ወደዚያው ነው የማመራው የሚል ጽኑ አቋም እንዳላት ይታወቃል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዚህ ወቅት ከኢራን ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ምንአልባትም ዛሬ ረቡዕ ከስምምነት ላይ ይደረሳል የሚል እምነት እንዳለ እየተገለጸ ነው፡፡

ኢራን ከየካቲት 21 አንስቶ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በጦርነት ውስጥ ነው የምትገኘው፡፡ ምንም እንኳን ጦርነቱ እንደተጀመረ አሜሪካ ጦርነቱን በጥቂት ጊዚያት ውስጥ እንደምትቋጨው የተናገረች ቢሆንም ነገሮች እንደተባሉት አልተጓዙም፡፡

በቀላሉ ትንበረከካለች የተባለችው ኢራንም ለአምስት ወራት ያህል እየተዋጋች ቀጥላለች፡፡ በርግጥ የደረሰባት ኪሳራ ቀላል የማይባል እንደሆነ የማይታመን ቢሆንም ይህን ያህል ጊዜ ግን ጦርነቱን መዋጋት ትችላለች የሚል ግምት አልተሰጣትም ነበር፡፡

ኢራን ወደዚህ ጦርነት ከመግባቱ በፊት አሜሪካን ከ20 ዓመታት በላይ ስታጠናት ቆይታ የገባችበት ጦርነት እንደሆነም ከዚህ ቀደም ገልጻለች፡፡

አሜሪካም ብትሆን ቀላል የማይባል ኪሳራ በዚሁ ጦርነት እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ የሰው ሃይል ኪሳራዋን ስንመለከት 17 ወታደሮቿ ሲገደሉባት 600 የሚሆኑት ደግሞ በዚሁ ጦርነት ቆስለውባታል፡፡ አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን አሸማጋይነት ሚዚያ ላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡ ይሄው ስምምነትም ዘላቂ ሰላም ያወርዳል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም እስካሁን ግን ሊሳካ አልቻለም፡፡

ኳታር ከሌሎች አሸማጋዮች ጋር በመሆን ለአምስት ወራት ያህል የዘለቀውን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe