ኢቲቪ የቴሌቪዥን ግብርን በእጥፍ ሊያሳድግ ነው

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለዓመታት ሲሰበስብ የቆየውን ዓመታዊ የቴሌቪዥን ባለቤትነትና ፈቃድ ግብር ከዚህ ዓመት ጀምሮ በእጥፍ ማሳደጉ ተሰማ፤

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓመታዊ የቴሌቪዥን ግብሩን በክፍለ ከተሞችና በቅርንጫፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሲሰበስብ የቆየ ቢሆንም በበቂ ሁኔታ ክፍያው ለመሰብሰብ ባለመቻሉ ክፍያውን ከኤሌትሪክ ወርሃዊ ፍጆታ ጋር ለመሰብሰብ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አግልግሎት ጋር  ሰሞኑን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟ፤

ይህንን ለመከወን የሚያስችለውን የህግ ማሻሻያ አዘጋጅቶ ለፖርላማው  የህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበው ኢቢሲ በነገው እለት አዋጁ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፤

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ዓመታዊ የቴሌቪዥን ግብር በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አግልግሎት በኩል እንዲሰበሰብ የታቀደ ሲሆን ክፍያውም ከዚህ በፊት ከነበረው በእጥፍ አድጎ 120 ብር እንዲሆንና ደንበኞች በየወሩ እንዲከፍሉ ይደነግጋል፤

የኤሌትሪክ ደንበኛ የሆነ ግለሰብ ሁሉ ቴሌቪዥን አለው የሚለው የአዋጁ መንፈስ የቋሚ ኮሚቴውን ያነታረከ ሲሆን በተለይ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ በደሳሳ ጎጆ የሚኖሩ የኤሌትሪክ ደንበኞች በሙሉ የቴሌቪዥን ግብር እንዲከፍሉ ማስገደድ ፍትሐዊ እንዳልሆነ የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe