ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶ/ር ግርማው ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 40 ታዋቂ ምሁራንን እንዲመሩ ተሾሙ

ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ በላይ ዓለምን እያስፈራት ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዳይ፣ ዛሬ በአንድ ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት እጅ ላይ ወድቋል። ይህ ወጣት አዕምሮ፣ ከሀርቫርድ እስከ ኦክስፎርድ፣ ከማይክሮሶፍት እስከ IBM የጥበብ ማማዎች ላይ ተራምዶ፣ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) መንበር ላይ ተሰይሟል!
የሳይንሱ ኮከብ ጉዞ
• የማይክሮሶፍት ኩራት፦ በ “AI for Good” ላቦራቶሪ ውስጥ ዓለምን የሚለውጡ ምርምሮችን ሲመራ ቆይቷል።
• የኦክስፎርድና ሀርቫርድ አሻራ፦ ማሽኖች ለሰው ልጅ ጤና እንዴት እንደሚሠሩ በሚያስደምም ጥልቀት የመረመረ ባለሙያ።
• የዕውቀት ጎተራ፦ ከ27 በላይ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ምርምሮችን ለዓለም ያበረከተ የዘመኑ ጥቁር አልማዝ።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአውሮፓውያኑ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፉት ታሪካዊ ውሳኔ፣ ዶ/ር ግርማው ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 40 ታዋቂ ምሁራንን እንዲመሩና እንዲያስተባብሩ በይፋ ሾመዋቸዋል።
“ኢትዮጵያ በዲጂታል 2030 ጉዞዋ ላይ ሳለች፣ እንዲህ ያለውን ‘ባለምጡቅ አዕምሮ’ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ መላኳ ለሀገር ትልቅ ኩራትና ለቀጣዩ ትውልድ ደግሞ ተስፋ ነው!”
ግርማው አበበ (ዶ/ር) በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት፣ ይህን አስፈሪ የተባለለትን ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ሰላምና እድገት እንዲውል በማድረግ ረገድ የዓለምን መሪ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe