ይህ ገንዘብ የሀገር ውስጥ ባንኮች ሲቋቋሙ ከሚጠየቁት አምስት ቢሊየን ብር ጋር ተቀራራቢት ያለው ነው፡፡
በተጨማሪም ስለ ገንዘቡ ምንች የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋልም ተብሏል፡፡ እነዚሁ የውጭ ባንኮች ሰብሲደሪ በመክፍፈት፡ቅርንጫፍ በመክፈት፡የውክልና ቢሮ ኖሯቸው እንዲሁም ኢትዮጽያ ውስጥ ካሉ ባንኮች አክሲዮን ወይም ድርሻ በመግዛት በአራት መንገዶች እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
የውጭ ባንኮች ኢትዮጽያ ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መፅደቁ ይታወሳል፡፡ የአዋጁን መውጣት ተከትሎም የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ተደርጓል፡፡

