ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት 11 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም 11 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ፤የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የኩባንያውን የሥድስት ወራት ስራ አፈፃፀም በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ በአጠቃላይ 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ኩባንያው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ እቅዱን በላቀ አፈጻጸም ማጠናቀቁን የገለስጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ  በበጀት አመቱ አጋማሽ የደንበኞቹን ብዛት 74.6 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዱን 98.3% እንዲሁም 42.86 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 98% ማሳካት ችሏል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 84.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 109% ያሳካ ነው፡፡
ኩባንያው የገቢ አማራጮችን ለማስፋት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረቶች በተጨማሪ ወጪን በአግባቡ ለመጠቀም ተግባራዊ ባደረገው (DO2SAVE) ስትራቴጂ በግማሽ አመቱ ብቻ ከብር 2 ቢሊዮን በላይ በመቆጠብ የዕቅዱን 113% አሳክቷል፡፡ ይህም ኩባንያው ትርፋማ እንዲሆን ለምናደርገው የጋራ ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሠረት ከውጪ ኦዲት ምርመራ በፊት ያልተጣራ ትርፍ (EBITDA) ብር 19.77 ቢሊዮን (46%) በማግኘት የእቅዱን 137% ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ በግማሽ ዓመቱ ብር 11 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ የተመዘገበ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14% እድገት ሲኖረው የትርፋማነት መጠኑን ወደ 26% ያደርሰዋል፡፡
የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ደግሞ 41 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱንም ነው የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፡፡ 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር በቴሌ ብር መንቀሳቀሱንም አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe