ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ 75 ሺህ ተማሪዎች የሚሆን 9መቶ ሺህ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።
በደብተር ድጋፉ 9መቶ30 ትምህርት ቤቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለትም “ለነገ ተስፋዎች” በሚል በቡራዩ ክፍለከተማ ለኩ ከታ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።
ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም ከ16.7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በመላው የአገራችን ክፍል በሚገኙ 28 የበጎ አድራጎት ማዕከላት ውስጥ ለሚገኙ ከ8ሺህ በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት ማድረጉንም ገልጸዋል።
ባለፈው አመት በተመሳሳይ በ26 የበጎ አድራጎት ማዕከላት ለሚገኙ ከ7ሺህ በላይ ዜጎች የምገባ መርሃ ግብር ማካሄዱንም አስታውሰዋል።
ኩባንያው በተጠናቀቀው በጀት አመት ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከ694 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ ማድረጉንም ወ/ሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

