ኢትዮ ቴሌኮም ነባር የኮፐር መስመሮችን ወደ ፋይበር የመቀየር” ኢኒሼቲቭ” አስጀመረ

በዘንድሮው በጀት ዓመት 100 ሺ የኮፐር ደንበኞቹን ወደ ፋይበር እንደሚያዛውር ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ነባር የኮፐር መስመሮችን ወደ ፋይበር በመቀየር ዘመናዊ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ሀገር አቀፍ (Copper Switch-off) ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
ኢኒሼቲቩ የባለገመድ የቴሌኮም አገልግሎት ደንበኞችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ከነባሩ የኮፐር መስመር ወደ ፋይበር በመቀየር እንደፍላጎታቸው እስከ 50ጊ.ባ በሰከንድ የሆነ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ 60ሺህ በክልል ከተሞች ደግሞ 40 ሺህ በድምሩ 100 ሺህ ደንበኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
በአዲሱ የፋይበር መስመር በኮፐር መስመር ያጋጥሙ የነበሩ የብልሽት ድግግሞሽን በመቀነስ ጥራት ያለው አገልግሎት ከማቅረብ ባሻገር ለደንበኞች ከፍተኛ ፍጥነት የሚፈልጉ (Ultra-low latency) አስተማማኝ የስማርት ሆም፣ ጤና፣ ኢንተርቴይመንት፣ ቪዲዮ ኮንፍራንስ የመሳሰሉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል።
ይህ ግዙፍ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ በምእራፍ ተከፍሎ በመላ ሀገራችን የሚከናወን ሲሆን ግለሰቦች እና ተቋማትን በፈጣን እና ዘመናዊ የፋይበር ኔትወርክ በማስተሳሰር የላቀ የቴሌኮም እና ዲጂታል ሶሉሽኖች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የበኩሉን ቁልፍ ሚና ለመጫወት የሚያስችል ግዙፍ አቅም ይፈጥራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe