ኤርትራዊያን ስደተኞች ጎረቤት ሀገር ወደ ሆነችው ኬኒያ ለመግባት በሚያደርጉት የሃይቅ ላይ ጉዞ ብዙዎቹ ህይወታቸውን እያጡ እንደሆነ ተሰማ፡፡
የኬኒያ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተሞች ላይ እያደረገው ባለው ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ስደተኞች በቱርካና ሃይቅ በኩል አድርገው መግባትን ምርጫቸው አድርገዋል፡፡
ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በሀገራቸው ያለውን የፖለቲካ እና የሃይማኖት ጫና ሽሽት ወደ ኬኒያ እና ዩጋንዳ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ብዙዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እየሞቱ እንደሆነ ተገልጻል፡፡
በኤርትራ ባለው የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ለማምለጥ በሚል ወጣቶች ወደ ኢትዮጽያ ድንበር በመግባት ወደ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ይሰደዳሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በኬኒያ በሚገኜው የቱርካና ሃይቅ ህይወታቸውን የሚያጡ ስደተኛ ኤርትራዊያን ቁጥራቸው ጨምሯል፡፡
ታዳጊዎች ከብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ግዳጅ ለማምለጥ ሲሉ ህይወታቸውን ለከባድ አደጋ አጋልጠው ይሰደዳሉ፡፡
ይሄው የውትድርና አገልግሎት ለረጅም ዓመታት ሊቆይ የሚችል ሲሆን፤በቆይታቸውም የግዳጅ የጉልበት ስራንም ያካትታል፡፡
በእግርና በመኪና በኬኒያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍል ውስጥ ወደ ሚገኘው ወደ ቱርካና ሃይቅ ዳርቻ ከደረሱ በኋላ ወደ ናይሮቢ ለመሻገር 1ሺ500 ዶላር ለሰዎች አዘዋዋሪዎች በመክፈል በአነስተኛ የእንጨት ጀልባ ለመሻገር ይሞክራሉ፡፡
በዚህን ስዓት አብዛኞቹ በሃይቁ ላይ እንደሚሞቱ ነው የተሰማው፡፡
በቅርብ ጊዜ በዚሁ ሃይቅ ዳርቻም በርካታ የኤርትራዊያን ስደተኞች አስክሬን ሲንሳፈፍ እንዳይዩ በሃይቁ ዙሪያ ያሉ አሳ አስጋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የሰዎች አዘዋዋሪዎቹ ወደ ናይሮቢ በሚያደርጉት ጉዞ በማሻገርና ቀጣይ ጉዟቸውም እስኪመቻች ድረስ እና አስፈላጊውን ክፍያ እስኪፈጽሙ ድረስ በማቆያ ቤቶች ማሳረፍን ያካትታል፡፡
በማቆያ ቤት ውስጥ ሲቀመጡ ስደተኞቹ የቤቱን ኪራይ እና ለምግባቸው ይከፍላሉ፡፡ ገንዘብ ጨርሰው በረሃብ የሞቱ ሦስት ወንዶች እና አንድ ሴት እንደምታውቅ በሰዎች ዝውውር ላይ ተሳታፊ የሆነች ሴት ለቢቢሲ ተናግራለች፡፡
በተጨማሪም እነዚሁ አዘዋዋሪዎች ለሟቾች ቤተሰቦች በህይወት እንዳሉ በመንገር ገንዘብ ሲቀበሉ እንደሚቆዩም ተነግሯል፡፡

