እስራኤል በየመን የሁቲ አማጺያን ላይ አዲስ ዘመቻ መጀመሯን ይፋ አደረገች

እስራኤል የመን እንደ ቴህራን ያለ እጣ ፈንታ ይገጥማታል በሚል ካስጠነቀቀች ወዲህ ነው ጥቁር ባንዲራ ብላ የሰየመችውን ዘመቻ መጀመሯን ያስታወቀችው፡፡

እስራኤል በየመን ወደቦች እና የኃይል ማመንጫ  ላይ የአየር ድብደባ ማድረሷንም ገልጻለች፡፡

እስራኤል የሃውቲ ቡድን በሚቆጣጠራቸው ሦስት የባህር ወደቦችና የሃይል ማመንጫ ጣቢያን በቦምብ ደብድባለች፡፡

ይህ እርምጃ ሃውቲዎች በእስራኤል ላይ ላደረሱት ተደጋጋሚ ጥቃት ምላሽ መሆኑን እስራኤል አስታውቃለች፡፡

እስራኤል በሁዳይዳህ፡ራስ ኢሳ እና ሳይፍ ወደቦች ላይ የፈጸመቻቸውን ጥቃት ተከትሎ ሁለት ሚሳኤሎች ከየመን መወንጨፋቸውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጻል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ እስረኤል ካትዝ ከጥቃቱ ኢላማዎች መካከል ጋላክሲ ሊደር የተሰኘችውና ከሁለት ዓመት በፊት በቡድኑ ቁጥጥር ስር የዋለችው መርከብ እንደምትገኝበት ተናግረዋል፡፡

የሃውቲ ቃል አቀባይ ጥቃቱን መሰረት አድርጎ በርካታ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ትላንት ምሽቱን የእስራኤልን ጥቃት ሲመክቱ ማደራቸውንም አስታውቀዋል፡፡

እስራኤል ካትዝ የአሁኑ ጥቃት የጥቁር ባንዲራ ዘመቻ አካል መሆኑን ጠቅሰው ሁቲዎች  ለድርጊታቸው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤልን ለመጉዳት የሚሞመክር ሁሉ ይጎዳል፤የየመን እጣ ፈንታ ከቴህራን እጣ ፈንታ ጋር ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በእስራኤል ላይ እጁን ያነሳ ሁሉ እጁን ይቆረጣል በማለት በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በአንጻሩ የሁቲ ባለስልጣናት እኛንና ሀማስን የሚያጠቃ በሰላም ሊተኛ አይችልም ብለዋል፡፡

የጋዛ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ የሁቲ አማጺያን ለፍልስጤማዊያን በመወገን ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ከማስወንጨፍ በተጨማሪ፤በቀይ ባህር የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት በማድረስ ይታወቃሉ፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe