እስራኤል የጋዛው ጦርነት ሃማስ መሳሪያውን እስካላስረከበ ድረስ መቋጫ እንደማይኖረው ገለጸች

ቡድኑ ትጥቁን የሚፈታበት ሁኔታ ተፈጠረ ማለት እስራኤል የዓለም ዋንጫን አነሳች ማለት ነው ሲሉ የሀገሪቱ ነባር ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

እኚሁ ሚኒስትር አሁን የጋዛው ጦርነት አላበቃም ምክንያቱም ሃማስ ትጥቁን አላስረከበም ብለዋል፡፡ ጦርነቱ አላበቃም አሁን ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ሌላኛው ምዕራፍ ለመግባት እራሳችንን ለማዘጋጀት የሚረዳ ነው እንጂ ሙሉ በሙሉ ቡድኑ መሳሪያውን እስካላስረከበ ድረስ ጦርነቱን አይቋጨውም ብለዋል፡፡

በርግጥ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቱ ሲፈረም ቡድኑ ትጥቁን እንደሚያስረክብ እምነት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህ የማይሆን ከሆነም ሃማስ በሃይልም መሳሪያውን እንደሚያስረከብም ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን እኚሁ የእስራኤል ነባር ሚኒስትር ለእስራኤል ቱዴይ እንዳሉት ሃማስ የሊባኖሱን ሄዝቦላህን በመመልከት ትጥቁን ለመፍታት ላይስማማ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ሄዝቦላህ ለሀገሪቱ መንግስት የቀረበለትን የትጥቅህን አውርድ ጥያቄን ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ እስራኤል የቡድኑን መጠናከር የስጋት ምንጭ በመሆኑ በቡድኑ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ነች፡፡

እናም እስራኤል ቡድኑ ቅድመ ሁኔታዎችን የማያከበር ከሆነ የተደረሰው ስምምነት በየትኛውም ደቂቃ ሊጣስ እንደሚችል ነው የምትገልጸው፡፡

ያለ መሳሪያ ሃማስ ምንም እንደሆነ እስራኤል ታምናለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ እራሱን ከመቼውም ጊዜ በላይ እያጠናከረ እንደሚገኝ ነው የተሰማው፡፡

የቡድኑ መጠናከር ደግሞ ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለራሷ ሊባኖስንም ከባድ ፈተና እንደሚሆንባት እስራኤል በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

እንደተባለውም ቡድኑ አቅሙን በማጎልበት የሊባኖሱን የሲቪል አስታዳደር በማስወገድ መላው ሀገሪቱን መቆጣጠር እንደሚፈልግ ከእስራኤል ቱዴይ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe