ከ60 ዓመታት በላይ ስራ ላይ የነበረው የውጭ ዜጎችን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚከለክለው አዋጅ ሊሻር ነው፡፡
የኢትዮጽያ መንግስት ለ65 ዓመታት ያህል የውጭ ሀገር ዜጎች የመሬት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚያደርግ አዋጅ ጥሎ ነበር፡፡
ይህንን ህግ የሚሽር አዲስ አዋጅ ነው ወደ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው፡፡
ይህን ማድረግ ያስፈለገው የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጽ የውጭ ካፒታልን ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታት ነው፡፡
በተጨማሪም የቤት ልማትና ተደራሽነትን ይበልጥ ማነቃቃት እየሰፋ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና አቅርቦት ሚዛን በተገቢ መንገድ ለማስጠበቅ ይረዳል ተብሏል፡፡ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ለመሆን መመደብ ያለባቸው አነስተኛ የገንዘብ መጠንም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፍሯል፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ለመሆን ማንኛውም የውጭ ዜጋ የሊዝ ሙሉ ዋጋውን ጨምሮ ለአንድ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሙሉ ዋጋ ወይም ለመኖሪያ ቤት ግዥ የሚወስደው የገንዘብ መጠን ከ150ሺ ዶላር ያላነሳ መሆን አለበት ይላል፡፡
በተጨማሪም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ለመሆን ከተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆን እንደሚገባው ሰፍሯል፡፡/

