ክኖር “ምርጡ ጉርሻ” ሲል የሰየመውን የንቅናቄ ዘመቻ ታላላቅ እንግዶች በተገኙበት ይፋ አደረገ

ክኖር ፤ “ምርጡ ጉርሻ” የተሰኘ አዲሱን የንቅናቄ ዘመቻውን በዛሬው ዕለት በቃና ዌርሀውስ ባዘጋጀውና በአረንጓዴ ምንጣፍ በደመቀው ዝግጅት ላይ ይፋ አድርጓል።

ይህ ዘመቻ ይፋ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በኢትዮጵያውያን የአመጋገብ ስርዓት ውስጥ የአትክልት ምግቦችን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅ የተነደፉ ተከታታይ አሳታፊ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ፤ ተከታታይ ሁነቶቹም ይህን ትልቅ ተነሳሽነት በማጉላት ረገድ ተደማጭነት ያላቸውን ግለሰቦችና ታዋቂ ሰዎችን ባንድነት አስተባብሯል።

ዩኒሴፍ እና ጤና ሚኒስቴር ያደረጉት ጥናት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ 39% የሚሆኑት አምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት የመቀንጨር ችግር የሚያጋጥማቸው ሲሆን ፤ ይህም ሥር በሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚመጣ መሆኑ ተመላክቷል።

የ #ምርጡ_ጉርሻ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን የአትክልት ምግቦችን በገበታቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ጥሪ ሲያቀርብ ፤ ልዩ የሆነውን የጉርሻ ባህል አካታች በማድረግ ነው።  ይህም ኢትዮጵያውያን ጣፋጭ የአትክልት ምግቦችን አብስለው እንዲመገቡ እና ለወዳጆቻቸው የአትክልት ምግብን በጉርሻ እንዲጋብዙ በማነሳሳት እና ውጤታማ ለውጥ በማምጣት በህብረተሰቡ ውስጥ ተጨባጭ ልዩነት ለመፍጠር ያለመ ነው።

የዩኒሊቨር አፍሪካ ኑትሪሽን ፕላትፎርም ዳይሬክተር ሰላመክርስቶስ በላይ “ምርጡ ጉርሻ’ ዘመቻ አዎንታዊ ምላሽ በማግኘቱ እጅግ ተደስተናል።” ያሉ ሲሆን ፤ አክለውም “ይህ ተነሳሽነት የአትክልት ምግቦችን የኢትዮጵያውያን ገበታ አካል ለማድረግ እና የተሻለ የአመጋገብ ባህልን አብሮ በመብላት ውስጥ ከፍ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳያል” ብለዋል።

ክኖር ንቅናቄውን ለመምራት ከታዋቂው ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ጋር በጋራ እየሰራ ነው። ኮሜዲያን እሸቱ የ”ምርጡ ጉርሻ” ዘመቻ ዋና መሪ እንደመሆኑ መጠን ፤ ዜጎች የአትክልት ምግቦችን ጠቃሚነት እንዲረዱ እንዲሁም አትክልት ምግቦችን እንዲጎራረሱ አነሳስቷል።

በዝግጅቱ አስደሳች የጉርሻ ሁነቶች የታዩበት ሲሆን፣ ተሳታፊዎች የአትክልት ማዕድ ተጋርተዋል። በዚህም ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህል እና የምግብ አሰራር ልምድን ያጎላ ሆኖ ታይቷል። ይህ አስደናቂ መስተጋብር ታዳሚዎችና ሰፊው ማህበረሰብ ከአትክልት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያስታውሳቸው ሁነቶቹ በልዩ ልዩ ፎቶግራፎች ተከትበዋል።

በዘመቻው  ተሳታፊዎች ሲጎራረሱ ፎቶዎችን የተነሱ ሲሆን በዚህም # ምርጡ ጉርሻ ለብሩሕ ኢትዮጵያ! በሚል አትክልት ምግቦችን የገበታችን ኩራት የሚደረግን ቅስቀሳ አበረታተዋል።
ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ: በዓለም ዙርያ በ190 ሀገራት ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ዩኒሊቨር፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውና አቅምን ባማከለ ሁኔታ ተደራሽ መሆን የሚችሉ የጋራ ንጽሕና መጠበቂያዎች፣ የግል ንጽሕና መጠበቂያዎች እና ምግቦችን የሚያመርት ግዙፍ ተቋም ነው፡፡

ዩኒሊቨር በዓለም ደረጃ፣ ከ130 ዓመታት በላይ አሻራውን ያሳረፈ ሲሆን ዓለም አቀፋዊውን ኢኮኖሚ በማነቃቃትና የሥራ አጥነት መጠንን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በዚህም ምክንያት ለተከታታይ ዓመታት በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ሥራ ቀጣሪ ተብሎ ተሰይሟል።

በ2007 ዓ.ም ዩኒሊቨር በኢትዮጵያ በርካታ ግቦችን ይዞ ቢሮውን ያቋቋመ ሲሆን በሁለተኛው ዓመት ሰኔ ወር ላይም ኩባንያው በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የማምረቻ ፋብሪካውን በይፋ አስመርቋል። በዚህ የዱከም ፋብሪካውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፉና እንደ ላይፍቦይ ሳሙና፣ ኦሞ፣ ክኖር አንኳር፣ ሰንላይት ሳሙናና የዱቄት ሳሙና እንዲሁም ሲግናል የጥርስ ሳሙና ያሉ የዩኒሊቨር ምርቶችን ያመርታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe