ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል።

እንዲሁም ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የትግራይ ክልል የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወስኖላቸዋል።

በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የክልሉ የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና በመዝገቡ 8ኛ ተጠርጣሪ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ዐቃቤ ህግ ለከፈትኩት የምርመራ መዝገብ የሚያስጠረጥር በቂ ማስረጃ ባለማግኘቴ በዋስ ይለቀቁ ሲል ለፍ/ቤት አመልክቷል።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ ቅዱሳን ነጋና ሌሎች የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ህግ ለፍ/ቤቱ አመልክቷል።

ጉዳዪን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው መሠረት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ እያንዳንዳቸው በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ አዟል።

አቶ ስብአት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እንዲታይና እስከዛው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል::

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe