ዋን ኤም. አር.ኦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አይሮፕላን የመጠገን ፈቃድ ያገኘ የግል ተቋም ሆነ

ዋን ኤም. አር.ኦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አይሮፕላን የመጠገን ፈቃድ ያገኘ የግል ተቋም ሆኗል።

በአሁን ሰዓት ናይጄሪያ ላይ መሰረት አድርጎ በምዕራብ አፍሪካ ለሚገኙ የግል ኦፐሬተሮች የጥገና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ዋን ኤም.አር ኦ. የተሰኘው የጥራት ማረጋገጫና ደህንነት ተቋም የጥገና ፈቃድ ሰርትፊኬት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አግኝቷል።

ተቋሙ ፈቃዱን ያገኘው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጃቸው አምስት ዓለም አቀፍ መስፈርቶች  ተመዝኖ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ዛሬ በነበረው የሰርተፊኬት አሰጣጥ መርሐግብር ላይ ተገልጿል፡፡

የጥገና ፈቃዱ ቦይነግ 737 ክላሲክና ቦይንግ 737 ኔክስት ጄኔሬሽን የተባሉ ዘመናዊ አይሮፕላኖችን ለመጠገን የሚያስችል እንደሆነ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 12 የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የግል አየር መንገዶች ያሉ ሲሆን እነሱን የሚያስተናግድ ሀንጋር ባለመኖሩ አይሮፕላን ለማስጠገን ወደ ኬንያ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችና አውሮፓ ጭምር በመሄድ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጉ ነበር ተብሏል።(ቲክቫህ መጋዚን)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe