በየዓመቱ በካናዳ ቶሮንቶ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ ስኬት ያስመዘገቡ፣ ለሀገርና ለማህበረሰብ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያንን የሚያከብረው በጀግናው አትሌታችን አበበ ቢቂላ ስም የተሰየመው የቢቂላ አዋርድ፣የ2026 ታዋቂ ግለሰቦችንና ተቋማትን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
የቢቂላ አዋርድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በኃይሉ አጥናፉ ለቁም ነገር ሚዲያ በላኩት መግለጫ የ2026 ዓመታዊው የቢቂላ አዋርድ ስነ-ስርዓቱ ቅዳሜ፣ (September 26, 2026) ዳንኤል ስፔክትረም (Daniels Spectrum) ቶሮንቶ፣ በካናዳ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ Yሚካሄድ ይሆናል ፡፡
በዕለቱ የካናዳ ፓርላማ አባልና የማህበረሰብ ተሟጋቿ ክብርት ዶሊ ብይግዩም በዋና ተናጋሪነት የሚገኙ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩን ደግሞ አንጋፋው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ በዋና አቅራቢነት ይመሩታል ተብሏል።
በዘንድሮው የቢኪላ አዋርድ ዕውቅና የሚያገኙ ተሸላሚዎች፦
* ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ (ከሞት በኋላ)፦ ለአፍሪካ ጥበብና ባህል ላበረከቱት አስተዋጽኦ
* አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (የሳንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መሥራች)፦ የሕይወት ዘመን ዕውቅና
* አና ጌታነህ (የ አፍሪካን ሞዛይክ መሥራች)፦ የሙያ ብቃት ዕውቅና
* ዶክተር ምህረት ደበበ (የቀድሞ የኢ.ኤ.ኃ.ኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ)፦
* ገዛሁ በቀለ (የ Green Care Naturals መሥራች)፦
* አዶናይ በርሃነ ሀይለሚካኤል ፡- በዲጂታል ሚዲያና በማህበራዊ ዘርፍ በወጣቶች ዘንድ የቲክቶክ የይዘት ፈጣሪ የዓመቱ የ«Youth Impact Award» አሸናፊ፤
* አብነት ታደለ (የ AGCEO መሥራች)፦ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ተሸላሚ(Community Service Excellence Award)
* በ GTA የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ፦ (Community Service Excellence Award)
የትምህርት ብቃት አሸናፊዎች
* ቢኤምነት አስፋው፣ * ኦሊያድ ሩንዳሳ፣* ናትናኤል ተሾመ፣* ኤደን በላይ እና ዮምኒ መኮንን ሆነዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህንና በስራ ፈጠራ ዘርፍ የሞፈር ኮፊ ባለቤት ሚልኪያሰ ተፈራ ከተሸላሚዎች መሀከል እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

