የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚየር ዘለንስኪ ሞስኮ ከሁለት ሀያላን ሀገራት ጋር በመተባበር እያጠቃችን ነው አሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ዩክሬን በጦር ሜዳው እጅግ እየበረታች ቢሆንም ፑቱንን ግን ማስቆም አልቻልንም ብለዋል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚየር ዘለንስኪ ሩሲያ ከኢራን ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር እያጠናከረች መጥታለች ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ሩሲያ ከሰሜን ኮርሪያ እና ቻይና ጋር ያላትን ትብብርም እያጠናከረች መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከእስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ኢንተርቪው ሰሜን ኮሪያ 30ሺ ወታደሮችን ለሩሲያ ልካለች ያሉ ሲሆን፤ኢራንም ተጨማሪ ሚሳኤሎችን በመላክ ድጋፍ ማድረጓን ቀጥላለች ብለዋል፡፡ ቻይናም ብትሆን የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትብብር እያደረገች ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢራን የጦር መሳሪያ ለሩሲያ በመላክ የጦርነቱ አካል ሆናለች ብለዋል፡፡ እኛ አዲስ የጦር ግንባር ላለመክፈት ጥረት እያደረግን ነው ነገር ግን ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ እኛን በማጥቃት ላይ ናቸውም ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩክሬን በካስፒያን ባህር ላይ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሊ ኢራን እርምጃ እንደምትወስድ አንስጠንቅቃል፡፡ ቴህራን በእኔ ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሙሉ የአጸፋ ጥቃት አለው አሜሪካ እና እስራኤልም ይህንን በሚገባ ያውቁታል ብላለች፡፡
ዘለንስኪ ሀገራቸው የምታመርተው የጦር መሳሪያ እየጨመረ መምጣቱንና በሩሲያ ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም እየጨመሩ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን አሁንም ቢሆም የፕሬዝዳንት ፑቲንን ጥቃት ለመከላከል የአቅም ውስንነት አለብን ብለዋል፡፡ እናም የአየር መከላከያ ስርዓት እርዱንና ከፑቲን ጥቃት አድኑን የሚል ይዘት ያለው ጥሪ አቅርበለዋል፡፡
ምዕራባዊያን አጋሮቻንን የአየር መከላከያ ስርዓት በመላክ እንዲሁም በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ በመጣል ዩክሬንን ማዳን እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአዲስ ወታደራዊ ጥቃት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ሩሲያ ከ300ሺ እስከ 500ሺ የሚደርሱ ወታደሮችን በማንቀሳቀስ አዲስ ጥቃት ለመፈጸም እቅድ እንዳላት ከደህንነት ተቋማት መረጃዎች ደርሰውኛል በማለት የታቀደውን ጥቃት ጠቁመዋል፡፡
ዘለንስኪ ከዚህ ቀደም ደጋግመው እንደገለጹት የአሜሪካው ፓትሮይት የአየር መከላከያ ስርዓት አሁንም ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የገባችበት ጦርነት ድጋፍ እንዳያገኙ መሰናክል መሆኑን ለእስካይ ኒውስ ተናግረዋል፡፡
ዘለንስኪ ይህን ያሉት ነገ በዋይት ሐውስ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ በተያዘላቸው ወቅት ነው፡፡
ዘለንስኪ እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአካል የተገናኙት በዚህ ወር መጀመሪያ በቱርክ የኔቶ ጉባኤ ወቅት ነው፡፡ በወቅቱም ዩክሬን ጦርነቱን ለማጠናቀቅ የሚያስችላትን እገዛ እንደምታገኝ ቃል ገብተውላቸውም ነበር፡፡//

