ዛምቢያዊቷ ባርብራ ባንዳ የዓመቱ ምርጥ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ተሸላሚ ሆነች

የስፔን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና አጥቂ አይታና ቦንማቲ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የአሜሪካ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ሳን ዲያጎ ተከላካይ ናኦሚ ግርማ ባለፈው ወር ይፋ በተደረገው የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ምርጫ ተሳታፊ የነበሩት የእግር ኳስ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች፣ የእግር ኳስ አመራሮች እና ጋዜጠኞች የ2023/24 የውድድር ዘመን ስኬትን ከግምት አስገብተዋል ተብሏል፡፡

በፓሪሱ ኦሊምፒክ ባርብራ ባንዳ ለሀገሯ አራት ግቦችን ያስቆጠረች ሲሆን÷ በአፍሪካ አኅጉር በኦሊምፒክ መድረክ 10 ግቦችን በማስቆጠርም ቀዳሚ ነች፡፡ ለኦርላንዶ ፕራይድ ባለፈው ዓመት ፊርማዋን ካኖረች ወዲህም 13 ግቦችን ማስቆጠር ችላለች፡፡

ተጫዋቿ ለመራጮቿ ብሎም ለቤተሰቧ እና ለክለብ አጋሮቿ ምስጋና በማቅርብ በዛምቢያ ተወልዶ በሴቶች እግር ኳስ ለዚህ ስኬት መብቃት ከባድ ነው ሆኖም ግን አድሬጌዋለው ብላለች፡፡ በቀጣይ ጠንክራ በመሥራት የላቁ ስኬቶች እንደምተስመዘግብ እምነቷን ገልጻለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe