የሁለት ዜናዎች ወግ ስለ አርበኞች ማህበር ህንጻ

“4 ኪሎ የሚገኘው የአርበኞች ማህበር ህንፃ ሊፈርስ ነው’ ቁም ነገር መጽሄት ጥቅምት 2013

‘ለአርበኞች መታሰቢያ በአጼ ኃይለ ሥላሴ የተገነባ ህንጻ፤ ቦታው “ለኮሪደር ልማት” በመፈለጉ ፈረሰ” ኢትዮጵያ ኢንሳይደር  ሰኔ 2016

አራት ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ህንፃ በአካባቢው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገነባው የህዝብ ቤተመፅሀፍት ህንፃ ግንባታ በሚል ሊፈርስ እንደሆነ ተሰማ፡፡
ከሰማኒያ ዓመት በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር በፋሽሽት ጣሊያን ወረራ ወቅት ታላላቅ ገድል ለሰሩ አባት አርበኞች መታሰቢያ እንዲሆን በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተቋቋመ ሲሆን አርበኞችንና የአርበኛ ቤተሰቦችን መብቶችና ጥቅም ለማስከበር በሚል ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ማህበሩ አቅመ ደካማ የሆኑ አባትና እናት አርበኞች ቤተሰቦችን ገቢ ለመደገፍ ህንጻ አገንብቶ እያከራየ በሚያገኘው ገቢ የሚተዳደር ሲሆን አሁን ከሚጠቀምበት ህንጻ በተጨማሪ አስር ያህል ኮንዶሚኒየም ቤቶች ከመንግስት ተሰጥቶት በማከራየት ገቢ እንደሚያገኝ ይታወቃል፡፡ አራት ኪሎ የሚገኘው የአርበኞች ህንጻ ባለ አራት ፎቅ ሲሆን በአካባበው በተጀመረው የህዝብ ቤተ መፅሐፍት ግንባታ ጋር በተያያዘ ቦታው ለማስፋፊያነት ስለሚፈለግ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ለማፍረስ  በቀድሞው አዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ተወስኖ የተፈረመበት ደብዳቤ  በአሁኗ ምክትል ከንቲባ ጠረጴዛ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች አመልክተዋል፡፡
የማህበሩ ህንፃ ሲፈርስ ሌላ ምትክ ቦታም ይሁን የህንጻ መስሪያ ገንዘብ የከተማ አስተዳደሩ ለማህበሩ ስለመስጠቱ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፤ በዚህ ዓመት የከተማ አስተዳደሩ በያዘው የ2013 በጀት ዝርዝር ውስጥ የአርበኞች ህንጻ ካሳ ጉዳይ በጀት እንዳልተያዘለትም ታውቋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተጠይቀው ስለተባለው የመስተዳድሩ እቅድ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ገልፀው የማህበሩ ህንጻ ታሪካዊ በመሆኑና አራት ኪሎ ከሚገኘው የድል ሀውልት ጋር የተቆራኘ ታሪክ ያለው በመሆኑ መስተዳድሩ ህንፃውን ያፈርሰዋል የሚል እምነት እንደሌላቸውና ቦታው የሚፈለግ ቢሆን እንኳ ማህበሩ አስቀድሞ ሊያውቀው እንደሚገባ ለቁም ነገር መፅሔት ተናግረዋል፡፡

ቁም ነገር

ያለ ማህበሩ እውቅና ህንጻውን ለማፍረስ የሚሞከር ከሆነ ከ43 ሺ በላይ የሚሆኑ አርበኞችና የአርበኛ ልጅ ልጆች የሚረዱበት የገቢ ምንጭ ስለሚቋረጥና የህልውና አደጋ ስለሚያጋጥም አስተዳደሩ ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲመለከተው አሳስበዋል፤
mmm
ለአርበኞች መታሰቢያ በአጼ ኃይለ ሥላሴ የተገነባ ህንጻ፤ ቦታው “ለኮሪደር ልማት” በመፈለጉ ፈረሰ
================================
ከጣሊያን ወራሪ ሰራዊት ጋር ለተፋለሙ አርበኞች መታሰቢያ እንዲሆን በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የተገነባው የአርበኞች ህንጻ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲፈርስ ተደረገ። ዘንድሮ 60 ዓመቱን የደፈነው ህንጻ እንዲፈርስ የተደረገው፤ ቦታው ለመንገድ ኮሪደር ልማት በመፈለጉ ምክንያት እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ከሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ይህ ህንጻ ንብረትነቱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ነው። ማህበሩ “የዐርበኞች ግንብ” በሚል ስያሜ በ1956 ዓ.ም ከተገነባለት ከዚህ ህንጻ ጎን፤ ሌላ ባለ አራት ወለል ህንጻ ከ13 ዓመት በፊት አሰርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል።
ማህበሩ በባለቤትነት ሲያስተዳድራቸው የቆያቸውን ሁለት ህንጻዎች ለቅቆ የወጣው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሐምሌ 3፤ 2016 እንደሆነ የማህበሩ ፕሬዝዳንት የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እዝራ ንጋቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የማህበሩን አንድ ህንጻ ተከራየቶ የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት፤ ከዚህ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ አገልግሎት ማቋረጡን ባወጣው ማስታወቂያ ይፋ አድርጓል።
ምድብ ችሎቱ በዚሁ ማስታወቂያው፤ የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ የተገደደው “ቦታው ለኮሪደር ልማት የሚውል” በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለማህበሩ በጻፈው ደብዳቤም፤ ህንጻዎቹ የሚፈርሱት “ቦታው ለልማት በመፈለጉ” እንደሆነ መጥቀሱን አቶ እዝራ ማስታወቃቸውን ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe