በጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ የተመሰረተውና ላለፉት 13 አመታት ሲካሄድ የቆየው ለዛ የኪነጥበብ ሽልማት በደመቀ ስነ ስርአት ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በሂልተን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በዚህ ዘርፈ ብዙ የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ባለብዙ ተሰጥዖው ንዋይ ደበበ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሲሆን ድምጻዊ ግርማ ተፈራ ካሳ ደግሞ የአመቱ ምርጥ አልበም አሸናፊ ሆኗል፡፡
ንዋይ ደበበ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በገለብና ሀመርባኮ አውራጃ በሀመር ወረዳ በ1953 ዓ.ም. ነው የተወለደው። በተወለደበት አካባቢ ትምህርቱን እስከ 4ኛ ክፍል ከተማረ በኋላ በ1963 ዓ.ም. ወደ አሰላ በመሄድ እዚያው እየተማረ ሳለ በአስተማሪውና በት/ ቤት ጓደኞቹ ዘንድ አድናቆትን እያገኘ መጣ። በኋላም ላይ ንዋይ በቤተሰቦቹ የሥራ ዝውውር ምክንያት ወደ ሲዳሞ ሄዶ አርባምንጭ ከነማና በወላይታ ሶዶ የቀበሌ ኪነት ውስጥ ድምፃዊ ሊሆን ችሏል።
ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በ1975 ራስ ቴአትር የተቀጠረ ሲሆን በ1977 ዓ.ም. የመጀመሪያ ካሴቱን ለማሳተም ችሏል። ንዋይ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪም የዘፈን ግጥሞችና የዜማዎች ደራሲ በመሆኑ አገራችን ካሏት ጥቂትና ልዩ ድምጻዊያን አንዱ ነው። ንዋይ ደበበ ከታዋቂ ዘፈኖቹ አንዱ «የጥቅምት አበባ» የተባለው ሲሆን ዜማውንና ግጥሙን የደረሰው ገና የ8ኛ ክፍል ተማሪ በነበረ ጊዜ እንደሆነ ይናገራል።
ንዋይ ደበበ ከድምጻዊነቱ ጎን ለጎን ለራሱም ሆነ ለበርካታ የሙያ አጋሮቹ ዜማና ግጥም በማዘጋጀት ይታወቃል።ታዲያ የንዋይ ድርሰቶች ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ሁኔታ ጆሮ ገብና ማራኪ፣ ተሰምተው የማይጠገቡ ዘመን ተሻጋሪ ናቸው። አብዛኛዎቹ የጥበብ ትሩፋቶቹ ብሩህ፣ አዎንታዊ፣ ተስፋ ፈንጣቂ ናቸው፤ ጨለምተኝነት አይጫናቸውም።
የዜማዎቹም ጭብጥ የሴትን ውበት፣ ፍቅርንና ናፍቆትን የሚገልጹ ናቸው። የቋንቋ ብቃቱ መገለጫ የቃላት ሀብታምነቱ፣ ረቂቅ ሐሳብን በሥዕል ከሳች፣ ገላጭና ተራኪ አቀራረብ ጋር በማሰናሰል አስገራሚውንና አስደማሚውም የግጥም ችሎታውን ጀባ ይላል። የግጥሞቹ አካሔድ ከዜማው ጋር ፍፁም የሚስማሙ፤ የማይጎረብጡ ናቸው። የራሱ የንዋይ የግል ቀለም ተብለው የሚለዩ፥ ንዋይ ጋር ብቻ የምናገኛቸው። የሥራዎቹን ጭብጥ ከተፈጥሮ ጋር በማያያዝም እንደንዋይ የተጠቀመ ድምጻዊ ያለ አይመስለኝም ይላል ታምራት አስታጥቄ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው የአድናቆት ጽሑፍ። በዚህ ረገድም ጨረቃ፣ ወንዝ ያፈራሽ፣ ማዕበል፣ መብረቅ፣ የበረሃ አውሎ ነፋስ፣ እንኮይ፣ መንደሪን፣ ሸንኮራ ተጠቃሽ ናቸው።
የንዋይ ሌላ መለያው ለአገሩ ያለውን ፍቅር ሲሆን ዘመን በማይሽራቸው ዜማና ነው ብሏል። ን ዋ ይ ሰ ሜ ን ከ ሠ ራ ቸ ው ዘፈኖች ውስጥ ከዘጠና በመቶ በላይ የራሱ ዜማና ግጥም መ ሆ ና ቸ ው ን ተናግሯል። ከ ን ዋ ይ ሙሉ የዜማና ግጥም ጎተራ ከ ተ ቋ ደ ሱ ት ድምጻውያን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ፤. ጸሐይ ዮሐንስ፤ ኤልያስ ተባበል፤ ሀመልማል አባተ፤ አስቴር ከበደ፤ መስፍን አበበ፤ ትዕግሥት ይልማ (“ሸጋ ጉብል በዐይኔ”)፤ ፋንትሽ በቀለ፤ኩኩ ሰብስቤ፤ሰላማዊት ነጋ (“ባንዲራችን”)፤ አስናቀ ገብረየስ (“ደራሽ”)፤. ደረጀ ደገፋው (“አበራሁኝ ሻማ”)፤ አቦነሽ አድነው፤ደሳለኝ መልኩ፤ ሰለሞን ተካልኝ፤ስዮም ዘውዴ፤ መስፍን በቀለ፤ ፀጋ ሙጬ ፤ አበበች ደራራ፤አስቴር ከበደ የጠቀሳሉ፡፡
በአጠቃላይ ንዋይ በአራት ዐሥርታት የጥበብ ጉዞው፥ ስምንት አልበሞችን ለብቻው እንዲሁም አምስት አልበሞችን ደግሞ በኅብረት ከሙያ አጋሮቹ ጋር የሠራ ሲሆን በተለያየ ጊዜ የለቀቃቸው በርካታ ነጠላ ዜማዎችም አሉት።
አርቲስት ንዋይ ደበበ የለዛ ሽልማት ላይ ተገኝቶ ከአንጋፋው የሙዚቃ ሰው ዳዊት የፍሩ እጅ እውቅናውን ከተቀበለ በኃላ “ዛሬ እኔን ለማክበር እዚህ የተገኛችሁ አድናቂዎቼ በሙሉ ከልብ አመሰናለሁ፡፡ አስታራቂም የለን እኛው እንታረቅ የሚለውን ዘፈን የጻፍኩት ለልጅነት ፍቅረኛዬ ነው፤ ግጥሞች አሽሞንምኖ በመሥራት ልዮ መታወቂያው እንዲሆኑ አድርጓል። አገሬ ናት ሀብቴ፣ ምንድን ነው ነገሩ ዘር ያልበቀለብሽ፣ አገሬን አልረሳም እና ኢትዮጵያ (ሲሳዬ ሲሳዬ) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ከኤች አይቪ/ኤድስ ጋር በተያያዘም ከአንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ጋር በወጣው ስብስብ የአልበሙ መጠሪያ የሆነው እንኖራለን ገና የንዋይ የአዕምሮ ጭማቂ ውጤት ነው።
ከንዋይ የቋንቋ ችሎታ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ በተለይ ግጥሞቹ በጣም እንደሚማርኳቸውና እንደሚያደንቋቸው ከመጥቀሳቸው ባሻገር በቋንቋ ምሁራን በሚገባ መጠናትና መተንተን አለባቸው ሲሉ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ተደምጠዋል። ታማኝ በየነም የሰይፉ ፋንታሁን እንግዳ በነበረበት ጊዜ የንዋይ የቋንቋ ችሎታ ሁሌም እንደሚያስገርመው ገልጿል።
ሥመጥሩ የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ በአንድ ወቅት ስለሚያደንቃቸው ዘፋኞች ሲጠየቅ “የንዋይንፈጠራ(creativity) በጣምአደንቃለሁ።ሐሳብናዜማየማያልቅበት በመሆኑካልገደብኩትበስተቀርከእሱጋር መሥራትአስቸጋሪነው”ብሏል።
ከሙያአጋሮቹመካከልከጥቂትወራት በፊትድምጻዊግርማተፈራከኢቢኤስጋር ነበረውቆይታየሴትልጅውበትንበዜማናግጥም በመግለጽንዋይንየሚያክልእንደሌለከታላቅ አክብሮትጋርምስክርነቱንሲሰጥሰምቼዋለሁ። ተወዳጁድምጻዊፀጋዬእሸቱበአንድወቅትንዋይ
መሸለምየሚገባውየባለብዙተሰጥዖመሆኑን በቁጭትገልጾ፥የሽልማትሰጪዎችመስፈርት ወቅታዊሆይሆይታየበዛለትንመሆኑአስተዛዛቢ አሁን ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር መንግስት ቢጠቀምበት እላለሁ፡፡ ከዚህ በሃላ ሙሉ እድሜዬን የኢትዮጵያ ህዝብን ሳገለግል መኖር ነው የምፈልገው ” በማለት ስሜቱን አጋርቷል፡፡ ይገባሃል!!! ሌላው የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ አልበም ተሽላሚ ድምጻዊ ግርማ ተፈራ ካሳ ነው፡፡በቀደመው ዘመን ልጆቻቸው አዝማሪና ዘፋኝ እንዳይባሉ አንካሴያቸውን ጨብጠው የሚቆሙ ወላጆችም ብዙ ነበሩ።
የሙዚቀኛው ካሳ ልጅ ግርማ ተፈራም ያለተቃውሞ አልነበረም ወደ ሙዚቃ ዘው ብሎ የገባው፡፡ የሙዚቀኛ ልጅ ነውና ያለጥርጥር ተቃውሞ አይኖረውም ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያ አልነበረም። ልጁ የእርሱን የእግር ዳና ተከትሎ ሙዚቀኛ እንዲሆን አባት ፍላጎትም ሆነ ምኞት አልነበረውም። የሚያስገርም ቢመስልም ያለ እናት ላሳደገ ሙዚቀኛ አባት ግን በተራ ምክንያት የሆነ አይደለም። እርሱም በእርግጠኝነት ባያውቀውም ሊሆን የሚችለው ምክንያት ግን ከሙያው ፍቅር ጋር መሳ ለመሳ የቆመውን የመገፋትን የመከራ ገፈት እንዳይቀምስ ነበር። አባት በሙዚቃ ገመድ እያለፈበት ባለው በዚህ ከመንደር እስከ ሀገር በተቆለለው ድካምና እንግልት በበዛበት ተራራ እንዲንገላታ ካለመፈለግ የመጣ ነበር። ለውሳኔውም የቤተሰብ ሸንጎ ከጠረጴዛው ዙሪያ ተሰይሞ መከረበት። የመጨረሻውን የግርማን የሀሞቱን ልክና የፈነቀለውን ወኔ ሲመለከት አባት ውሳኔውን መቀየሩ አልቀረም። እንግዲያውስ አለ አባት፤ እንደኔ በልምድ ሳይሆን በዕውቀት እንድትገባበት በማለት የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲገባ አደረገው። ግርማ ተፈራ ከድምጹ ባሻገር ዛሬም ድረስ የሚጠቀምበትን የህይወት ዘመን የሙዚቃ ዕውቀት የሸመተው የዚህን ጊዜ ነበር። የሙዚቃን ዕውቀተ ስጋ “ተታሎ አይሰጥ ስጋ” እያለ መቅኔውን ከአጥንቱ እየሰረሰረ ሲበላ ከርሞ በአራተኛው ዓመት የሙዚቃ ቆቡን ደፋ።
ከዚህ በኋላ ወደሚወደው ሙዚቃ በኩራት ሲመጣ የመጀመሪያ ሥራው ስለ አባት ያዜመው ዜማ እንደሆነ ይናገራል። በጣም ስለተወደደለት ትላልቅ ሆቴሎች ሳይቀሩ እየሄደ እንዲዘፍንላቸው በጥሪ ቢያጨናንቁትም ምቾቱን የነሳው ጉዳይ እየገጠመው ተቸገረ። ጥሪው ደርሶት ማይኩን ጨብጦ በቆመ ቁጥር ሊዝናና ከመጣው መሃል አባቱን እያስታወሰ ሆድ የሚብሰውን ሰው በተደጋጋሚ መመልከቱ ሥራው ቢቀርስ አስባለውና ተወት አደረገው።
እስከዛሬ ስለሠራቸው በርካታ የአልበምና የነጠላ ዜማ ሥራዎቹን ሳነሳ ስለ ድምጽና የአዚያዚያም ብቃቱ እያወራሁ ለቀባሪ አላረዳም። ቀልብን ከስሜት ጠፍረው ሽምጥ የሚያስጋልቡት ሙዚቃዎቹ ይናገራሉ። እንደ ሙዚቃ ግን፤ ግርማ የየትኛው ዘርፍ ተጫዋች ነው ብለን ካልን የአንድ ዓይነት ብቻ አለመሆኑ ነው። ከሥራዎቹ አኳያ ምድብ ከሰጠነው በአመዛኙ የሶል እና ሮክ ዓይነት ስልቶች ናቸው።
የአባቱ ልጅ የሆነው ግርማ ተፈራ አንድ የሙዚቃ ጎተራ ያለው ይመስላል።የራሱን አልበም ይዞ በመጣ ቁጥር ሁሉ ከዚህ ጎተራ ውስጥ እየዘገነ አንድና ሁለት ሙዚቃ የአባቱን ጨመር ያደርግበታል። “ሥራ ፈቶ ሲያይሽ ያንቺ ተመልካች፤ በውበት ቁንጅና ማን ነበር እንዳንቺ” በዚህ ሥራ ውስጥ ከእርሱ አልፎ ያለውን የአባቱን የተፈራ ካሳን ልክ አሳይቶበታል።ተፈራ ካሳ ያኔ ገና በክቡር ዘበኛ ባንድ ውስጥ ሳለ በማርሽ ባንዱ ታጅቦ የሠራው የዚህ ግሩም ዜማ ጥፍጥናው የሚጀመረው ገና ከሙዚቃው መግቢያ ላይ ነው። ከጅምሩ ነብስ ያስኮበልላል። በድጋሚ ግርማ ሲጫወተው ደግሞ ሙዚቃው የነበረው ውበትና ግርማ ኮለል እያለ ወጥቶ ኩልል ብሎ ታየ።“መቼ
ትመጪያለሽ” የሚለውንም የቀድሞውን ደምግባቱን ሳይገፍ ከነባንድ ትዝታው ጋር በቅርቡ አስደምጦናል። ቀድሞ ከነበሩበት አንጻር በተደራጁ የሙዚቃ መሳሪያዎች በማዋሃድ በዘመናዊ መልኩ ከማቅረብ በስተቀር እንዳሻው በመሥራት ኃላፊነቱን አልዘነጋም። ከራሱ ሥራዎች በተጨማሪ በየጊዜው ቆንጠር እያደረገ ድንገት
የሚያሰማን እኚህ ዜማዎች ከሙዚቃ ጋር በፍቅር እየጣሉ ፍቅርን የሚያሲዙ ናቸው። እርሱ እንደሆን አያልቅበት ነው፤ በዚህም አባቱን ዳግም እያስታወስን ግርማ ተፈራንም እያደነቅን እኛም እንዝናናለን።
የአባቱ ልጅ ማለት እንግዲህ ለዚህ ዓይነቱ ልጅ ነው ይላል ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ብርሃኑ “እርሱ ለኔ የተለየ ነው። ለርሱ ያለኝ ፍቅርም እጅግ ልዩ ነው። በህይወት ኖሮና ኖሮኝ ሁሉንም ነገር ባደርግለት ይሄን ፍቅሬን ብገልጥለት ደስ ይለኝ ነበር፡፡” የሚሉ የህይወት ዘመን ዐረፍተ ነገሮች አሉት። ይህ ታዲያ ለአባቱ እንጂ ለማንም አይደለም። የአባቱ መውደድ በልቡ ውስጥ ቃላት የማይቋጥሩት ስንኝ ነው። ደግሞ ስለ አባት አዚሟልና በዚያ የአባቶች ቀን ድምጹ እንደተስረቀረቀ ውሎ ያመሻል።ሁሉም ልጆች ከአባታቸው ጥላ ስር ግርማ ተፈራን አብረው እያስታወሱት ይውላሉ።
ከአባት የተሰጠ ምርጡ የአባት ስጦታና ግብዣ ነው። ግርማ መቼስ አባቱን ሲወድ ፍቅሩ ወሰን አልባ ዳርቻው ሞላ ነው።“ኖሮ ላሳየው አልቻልኩምና የእርሱን ጥሩነት የምመልሰው ለልጆቼ ጥሩ አባት በመሆን ነው” ይላል ለጥሩነት ምላሹ ጥሩነት መሆኑን ተገንዝቦ። “ግን የት ሀገር?” የወዲህኛው የቅርብ ሥራው ነው። ከአራት ዓመታት በፊት ያለቀለት የነበረ ሥራ ቢሆንም በኮቪድ ወረርሺኝና ጦርነቶች ሳቢያ የመምጫ ጊዜው ተራዝሞ ከርሟል። 2015ን ግን ለመቅረት አልቻለምና በማለቂያው ደረሰ።“የኖህ መርከብ” የሚለውን ዜማም በመጀመሪያዎቹ ላይ አክሎ መጣ።
በሙዚቃ ደረጃ ብቻ 20 ያህል ሙዚቀኞች ተሳትፈውበታል። የሚወደው ወዳጁ ማህሙድ አህመድና ቴዲ አፍሮም አንድ አንድ ሥራ ሰጥተውታል። ጥራቱን ለመጠበቅ ሙያዊ ጉልበትም ፈሶበታል። የአልበሙ መጠሪያ የሆነው ዜማም አንዲህ ነው፤
“በመልክሽ አይደል ወይ በቁንጅናሽ፤
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር፤
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሀገር?”
በግጥም ቴዲ አፍሮና ይልማ ገ/ አብ ተዋህደውበታል። ዜማውን ደግሞ ቴዲ አፍሮ ሲሠራው በሙዚቃ ቅንብሩ ደግሞ አቤል ጳውሎስ ተጠቦበታል፡፡ግርማ አዩኝ አእዩኝ የማይል ስራው ላይ የሚያተኩር ሙያተኛ ነው፡፡ የላዛ የአመቱ ምርጥ አልበም ሽልማቱን ከአንጋፋው የሙዚቃ ሰው ዳዊት ይፍሩ እጅ ሲቀበልም ብዙ መናገር አልቻለም፡፡ በጠቅላላው የሙዚቃ አድናቂዎቼን “አመሰግናለሁ” ነበር ያለው፡፡

