የትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ማሟላት ካልቻሉ አዳሪ ትምህር ቤት እንደሚሆኑ ገልጻል፡፡ ሚኒስቴሩ ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ቦታ በመስጠቱ ከግል ተቋማት ጋር ከአራት ዓመታት ጀምሮ እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ዳግም ምዝገባን በተመለከተም ባለፉት 3 ዓመታት ስለመስፈርቱ የማሳወቅ ስራ እንደተከናወነና የማያሟሉ በዘርፉ መቀጠል እንደማይችሉ ሲነገር መቆየቱን አስታውሷል፡፡
የግል ኮሌጆች እንዲዘጉ የተለየ የግል ምክንያት የለም ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ሳይማር ዲግሪ የሚሰጠው ተማሪ ግን ኢትዮጽያ ውስጥ እንዲኖር አይፈለግም ብሏል፡፡ በተጨማሪም ተመሳሳይ ግምገማ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይም ይደረጋል ብሏል፡፡ በዚሁ አሰራር መሠረት ይዘጋሉ ተብሎ የሚታሰቡት የግሎቹ ብቻ ሳይሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡
በዚህም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላት ካልቻሉ የሚኖራቸው ጥቅም ታስቦ፤ሰፋ ያለ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል መግለጹን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡//

