የሜትር ታክሲ ድርጅቶች የትራንስፖርት መቆጣጠሪያቸውን በሀገር ውስጥ እንዲያደርጉ ሊገደዱ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግስት አልታዘዝም ያሉ ጥቂት የሜትር ታክሲዎች መኖራቸውን ገለጸ፡፡

እነዚሁ ድርጅቶች የትራንስፖርት መቆጣጠሪያቸውንም በውጭ ሀገራት አድርገው እንደሚሰሩ ደርሼበታለሁ ማለቱም ተሰምቷል፡፡ በመሆኑም የሜትር ታክሲ ድርጅቶች የትራንስፖርት መቆጣጠሪያቸውን በሀገር ውስጥ እንዲያደርጉ ሊገደዱ ነው ይችላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አደረኩት ባለው ግምገማ አንዳንድ የሜትር ታክሲ ድርጅቶች ለመንግስት ባለመታዘዝ ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ ባህሪ እያሳዩ ነው፤የትራንስፖርት መቆጣጠሪጣቸውንም ከኢትዮጽያ ውጭ አድርገው እንደሚሰሩ ተረድቻለሁ ነው ያለው፡፡

ይህን ተከተሎም ከሜትር ታክሲዎች ጋር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በአሰራር ደረጃ ለመፍታት የሚያስችል መመሪያ እንደ አዲስ እየጸደቀ እንደሚገኝ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ቢሮው በሌላ በኩል ከዚህ በኋላ በመንግስትም ይሁን በግል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ተሸከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ብቻ እንደሚሆኑም ጠቁሟል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe